Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አምንሃለሁ

Amnehalehu

2011 · ትራክ 12 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ምነው ሰማያትን ቀደህ ብትወርድልኝ

ብዬ እኔ ስጣራ ታየኛለህ (፪x)

ለካስ ታየኛለህ ከሰማያት በላይ

ለእኔ የምትራራ ታየኛለህ (፪x)

ያልተጠባበኩት የክብርህን ስራ

ገልጸህ ልታሳየኝ ታየኛለህ (፪x)

አሁን ተረዳሁት ሁሉ ለበጐ ነው

የአንተ አላማ ገባኝ ታየኛለህ (፪x)

ታየኛለህ ስጠራህ ትሰማኛለህ

ታየኛለህ የልቤን ታደምጠኛለህ

ታየኛለህ የደምህ ኪዳን አለኝ

ታየኛለህ ላትጥለኝ ስለያዝከኝ

ኢየሱስ (፪x) (ኢየሱሴ) አንተ ነህ ለእኔ ዋሴ (ለእኔ ዋሴ)

ፍቅርህን አስባለሁ (ፍቅርህን አስባለሁ) ዘለዓለም እወድሃለሁ (ዘለዓለም ወድሃለሁ) (፪x)

አምንሃለሁ አትጥልም አንተ አትጐዳም

አምንሃለሁ ጀርባ አትሰጥም ደርሰህ እንደባዳ

አምንሃለሁ መጠጋት ማቀፍ ባሕሪህ

አምንሃለሁ ተመካሁ በማይጥል ፍቅርህ (፪x)

ኢየሱስ (፪x) (ኢየሱሴ) አንተ ነህ ለእኔ ዋሴ (ለእኔ ዋሴ)

ፍቅርህን አስባለሁ (ፍቅርህን አስባለሁ) ዘለዓለም እወድሃለሁ (ዘለዓለም ወድሃለሁ) (፪x)

አምንሃለሁ ታማኝ ነህ ከምንም በላይ

አምንሃለሁ ቃል ሳይሆን የልብን የምታይ

አምንሃለሁ እንደሰው አይተህ አተፈርድም

አምንሃለሁ መንገድ ላይ ጥለህ አትሄድም (፪x)

ምነው ሰማያትን ቀደህ ብትወርድልኝ

ብዬ እኔ ስጣራ ታየኛለህ (፪x)

ለካስ ታየኛለህ ከሰማያት በላይ

ለእኔ የምትራራ ታየኛለህ (፪x)

ያልተጠባበኩት የክብርህን ስራ

ገልጸህ ልታሳየኝ ታየኛለህ (፪x)

አሁን ተረዳሁት ሁሉ ለበጐ ነው

የአንተ አላማ ገባኝ ታየኛለህ (፪x)

ታየኛለህ ስጠራህ ትሰማኛለህ

ታየኛለህ የልቤን ታደምጠኛለህ

ታየኛለህ የደምህ ኪዳን አለኝ

ታየኛለህ ላትጥለኝ ስለያዝከኝ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ