አቀላልቷል ሰማዩ
Aqelaltual Semayu
2011 · ትራክ 2 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አቀላልቷል ሰማዩ ሊሰናበት ሌቱ
ምን ጭጋጉ ቢያይል አይቀርም መንጋቱ
ብርሃን ዘንበል ቢል ቢዳምን ደመና
አዲስ ቀን ያሳያል ጌታ ቸር ነውና (፪x)
አሃሃ አንተን ታምኖ ማንስ ወድቆ ቀርቷል
አሃሃ የታመነህ ሁሉን ጥሶ አልፏል
አሃሃ መመኪያ ነህ ለምስኪኑ ጋሻ
አሃሃ ማምለጫ ነህ ከጥፋት መሸሻ
የእኔ አባት የእኔ ጌታ
የእኔ ንጉሥ የእኔ አለኝታ
በድካሜ ያልሳቅክብኝ እምባዬንም ያበስክልኝ
ሳጸለቸኝ ተሸከምከኝ ከእናት ከአባት በላይ ሆንከኝ
ኢየሱስ (፫x) ከፍ በልልኝ (፪x)
አባት አለኝ እኔ ከአባትም አባት
ያዋጣኛል ብዬ ያላፈርኩበት ፤ ያላፈርኩበት (፪x)
እግዚአብሔር ከአየልኝ ከቶ አንድም አይጐድልም
አምላኬ ታማኝ ነው ሁኔታን አላይም
እጠብቀዋለሁ በስፍራዬ ሆኜ
ያለውን ያደርጋል ታማኝ ነው ጌታዬ
እግዚአብሔር ያለው ይሆናል
እግዚአብሔር ያለው ይጸናል
እግዚአብሔር ያለው ይሳካል (፪x)
አዝማች · Chorus
አቀላልቷል ሰማዩ ሊሰናበት ሌቱ
ምን ጭጋጉ ቢያይል አይቀርም መንጋቱ
ብርሃን ዘንበል ቢል ቢዳምን ደመና
አዲስ ቀን ያሳያል ጌታ ቸር ነውና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ