ዝርግፍ ጌጤ
Zergef Gietie
2011 · ትራክ 7 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ዝርግፍ ጌጤ ነህ ኩራቴ
ኢየሱሴ ማዕረጌ
ሁሉ በአንተ ሆነ በአምላኬ
ሁሉ በአንተ ሆነ በአምላኬ (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እንደዐይኖችህ ብሌን ተጠንቅቀህልኝ
የከበደ ሸክሜን ከእኔ አራግፈህልኝ
ቀና ብዬ እንድኖር አንተ አድርገኸኛል
ከክብር ጋር ስፍራን ጌታ ሰጥተኸኛል
የእኔ አባት የእኔ ጌታ
መመኪያዬ ነህ ጌታዬ
የእኔ አባት የእኔ ጌታ
ማረፊያዬ ነህ ጌታዬ
አዝማች · Chorus
ዝርግፍ ጌጤ ነህ ኩራቴ
ኢየሱሴ ማዕረጌ
ሁሉ በአንተ ሆነ በአምላኬ
ሁሉ በአንተ ሆነ በአምላኬ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔ ያላየሁትን አንተ አይተህልኝ
የሕይወቴን ጐዳና ያቀናናህልኝ
ከእኔ በላይ ለእኔ አንተ ታስባለህ
አላማህ መልካም ነው በእኔ ላይ ያለህ
የእኔ አባት የእኔ ጌታ
መመኪያዬ ነህ ጌታዬ
የእኔ አባት የእኔ ጌታ
ማረፊያዬ ነህ ጌታዬ
አዝማች · Chorus
ዝርግፍ ጌጤ ነህ ኩራቴ
ኢየሱሴ ማዕረጌ
ሁሉ በአንተ ሆነ በአምላኬ
ሁሉ በአንተ ሆነ በአምላኬ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ያሰብከው ሆነልኝ አንተ ለእኔ ያልከው
አንተ ይሁን ስትል ጌታ ከልካይ ነው
ያሰብከው ይሆናል ያየኸው ይጸናል
እንደ ቃልህ ሆነህ ታምነህ ተገኝተሃል
የእኔ አባት የእኔ ጌታ
መመኪያዬ ነህ ጌታዬ
የእኔ አባት የእኔ ጌታ
ማረፊያዬ ነህ ጌታዬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ