ኢየሱስ
Eyesus
2011 · ትራክ 14 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አይታለፍም ብዬ ደምድሜ ነበረ
ጌታዬ በአንተ ሁሉ ተውቦ ሰመረ
ምን ይሳንሃል ሁሉን ልጸራው ችለሃል
ተራራውንም ደልዳላ ሜዳ አርገሃል
ቁጥር 2 · Verse 2
(ኢየሱስ) ሕይወቴ ነህ አንተ
(ኢየሱስ) ትርጉም ማንነቴ
(ኢየሱስ) በቀኝህ ያኖርከኝ
(ኢየሱስ) የልቤ ኩራቴ
(ኢየሱስ) ምሥጋናዬ አንተ ነህ
(ኢየሱስ) አንተን እጠራለሁ
(ኢየሱስ) ስምህ ሲያለመልም
(ኢየሱስ) እንደሚፈስ ዘይት ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
አምላክ ሆይ በአንተ የማያልፍ የለም
ምርኩዜ አንተ ነህ ሸንበቆ አይደለህ
ትላንት ያደረከው እምነት ሆኖኛል
የማይጥል እጅህ እጄን ይዞኛል
አልተረታሁም እኔስ በስምህ ተወረርጄ
ፊቴ አላፈረም መልሴ ፈጠነ ገባልኝ ከእጄ
የማይቻለው በአንተ ተችሎ አይቼዋለሁ
ለስምህ ክብር ለጌትነትህ እዘምራለሁ
አዝማች · Chorus
አለኝ ወዳጅ የምለው ፤ አለኝ ውስጤ ሚወደው
አለኝ ሚስጥረኛዬ ፤ ሳይንቅ ገብቷል ጓዳዬ
አለኝ ወዳጅ የምለው ፤ አለኝ ውስጤ ሚወደው
አለኝ ሚስጥረኛዬ ፤ ኢየሱስ ገብቷል ጓዳዬ
ኢየሱስ ገብቷል ጓዳዬ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እረኛዬ ነህ ከአንበሳው ከድብ አድነኸኛል
አበቃ ሲባል የሁሉንም ቁልፍ ይዘህ ደርሰሃል
ታዲያ ብዘምር ከሆንኩት በላይ መች ይበዛና
ታሪኬ ሆነህ አዳፋ ልብሴን ጥለሃልና
አዝማች · Chorus
አለኝ ወዳጅ የምለው ፤ አለኝ ውስጤ ሚወደው
አለኝ ሚስጥረኛዬ ፤ ሳይንቅ ገብቷል ጓዳዬ
አለኝ ወዳጅ የምለው ፤ አለኝ ውስጤ ሚወደው
አለኝ ሚስጥረኛዬ ፤ ኢየሱስ ገብቷል ጓዳዬ
ኢየሱስ ገብቷል ጓዳዬ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ