መንፈስ ቅዱስ
Menfes Qedus
2011 · ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
መንፈስህን ከእኔ አትውሰድብኝ (፬x)
ከአንተ ሌላ ሌላ ሌላ ወዳጅ የለኝ
እንደ አንተ ሚሆንልኝ ከአንተ ሌላ ሌላ
ሌላ ወዳጅ የለኝ እንደ አንተ ሚሆንልኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
የውስጡ ቆሽሾ ውጪውን አጥርቼ
ትንኝ ያጠራው ግመል ያክል ውጬ
ለሰው ታይታ ሚኖር ፈሪሳዊ ሆኜ
ማለፍን አልሻም ከክብርህ ጐድዬ
አዝማች · Chorus
አቤቱ አምላኬ ሆይ
በፊትህ ራሴን ላሳይ
አግዘኝ እጠራሃለሁ
ቸር አምላክ ነህ አውቅሃለው (፪x)
አትተወኝ አትጣለኝ
ያላንተማ ሕይወት የለኝ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እንደልቤ ሳይሆን ልሁን እንደልብህ
ልወረስ በክብርህ እጄን ይያዝ እጅህ
መንፈስህ መሪዬ ይሁን እረኛዬ
በእቅፍህ ውስጥ ነው ክብሬም ዋስትናዬ
አዝማች · Chorus
አቤቱ አምላኬ ሆይ
በፊትህ ራሴን ላሳይ
አግዘኝ እጠራሃለሁ
ቸር አምላክ ነህ አውቅሃለው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
መንፈስ ቅዱስ የሕይወቴ ትርጉም ነህ
መንፈስ ቅዱስ የልቤ ማረፊያ
መንፈስ ቅዱስ ሌላ አልመኝም
መንፈስ ቅዱስ አጽናኝ ከአንተ ወዲያ
አዝማች · Chorus
አትተወኝ አትጣለኝ
ያላንተማ ሕይወት የለኝ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ