ምድረበዳው
Medrebedaw
2011 · ትራክ 3 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ምድረበዳው ተዐምር መሥሪያ ነው ፣
ባዶ ነገር ሙላትን ያያል ፤
ሰው አለቀ አበቃ ሲል ፣
የአንተ ተዐምር ይጀምራል
አየሁ በዐይኔ የአንተን በጐነት ፣
በቀን በሌት ክንድህ ሲረዳኝ ፤
በማዕበሉ በወጀቡ ላይ ፣
ከፊት ቀድመህ በድል ስትመራኝ (፪x)
አይቼሃለሁ ከወዳጅ ይልቅ ወዳጅ የሆንከኝ
አይቼሃለሁ አንተ ብቻ ነህ ክብር ያሳየኸኝ
አይቼሃለሁ ይሆናል ያልክልኝ ሆኗል በሕይወቴ
አይቼሃለሁ ድካሜን ሽረህ ሆንከኝ ጉልበቴ
ቁጥር 1 · Verse 1
ያሰበውን ያቀደውን በሕይወቴ ፈጸመና
ድንቅን ሰርቶ አስደነቀኝ የእኔ ጌታ እንደገና
አዲስ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ጽፎ ሰጠኝ ከሰማይ
እርሱ ካለ ሆነ እኮ ነው የለበት አዝዥ ከልካይ
በአንተ መታመኔ አዋጣኝ ጌታዬ
አላፈርኩብህም ያዋጣኛል ብዬ
ጠላቴም ወዳጄ ግርም እስከሚለው
ይሄው ተዐምርህን በዘመኔ አየሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምድረበዳው ተዐምር መሥሪያ ነው ፣
ባዶ ነገር ሙላትን ያያል ፤
ሰው አለቀ አበቃ ሲል ፣
የአንተ ተዐምር ይጀምራል
አየሁ በዐይኔ የአንተን በጐነት ፣
በቀን በሌት ክንድህ ሲረዳኝ ፤
በማዕበሉ በወጀቡ ላይ ፣
ከፊት ቀድመህ በድል ስትመራኝ (፪x)
አይቼሃለሁ ከወዳጅ ይልቅ ወዳጅ የሆንከኝ
አይቼሃለሁ አንተ ብቻ ነህ ክብር ያሳየኸኝ
አይቼሃለሁ ይሆናል ያልክልኝ ሆኗል በሕይወቴ
አይቼሃለሁ ድካሜን ሽረህ ሆንከኝ ጉልበቴ
ቁጥር 2 · Verse 2
በአንተ እጅ ነው ሁሉ ነገር
የሁሉ ቁልፍ የአንተ ብቻ
ይሁን ያልከው ሲሆንልህ አይቻለሁ የለህ አቻ
ሞተውን ያበቃውን ቃል አውጥተህ ትጥራለህ
ተዘጋው ደጅ ገብተህ ሰላምህን ታውጃለህ
በአንተ መታመኔ አዋጣኝ ጌታዬ
አላፈርኩብህም ያዋጣኛል ብዬ
ጠላቴም ወዳጄ ግርም እስከሚለው
ይሄው ተዐምርህን በዘመኔ አየሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምድረበዳው ተዐምር መሥሪያ ነው ፣
ባዶ ነገር ሙላትን ያያል ፤
ሰው አለቀ አበቃ ሲል ፣
የአንተ ተዐምር ይጀምራል
አየሁ በዐይኔ የአንተን በጐነት ፣
በቀን በሌት ክንድህ ሲረዳኝ ፤
በማዕበሉ በወጀቡ ላይ ፣
ከፊት ቀድመህ በድል ስትመራኝ (፪x)
አይቼሃለሁ ከወዳጅ ይልቅ ወዳጅ የሆንከኝ
አይቼሃለሁ አንተ ብቻ ነህ ክብር ያሳየኸኝ
አይቼሃለሁ ይሆናል ያልክልኝ ሆኗል በሕይወቴ
አይቼሃለሁ ድካሜን ሽረህ ሆንከኝ ጉልበቴ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ