Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አላፈርኩም

Alaferkum

2007 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አላፈርኩም አንተን ብዬ (፪x)

ዛሬም አለሁኝ ተደላድዬ

ከዚህ ዓለም ክፋት ፍቅርህ ለይቶኛል

የምህረትህ ብዛት ቤትህ አኑሮኛል

ታዲያ ከበርኩ እንጂ መች ከሰርኩኝ እኔ

የዘላለም አምላክ እያለ ከጐኔ (፬x)

ኢየሱስ አለ ከጐኔ

አላፈርኩም አንተን ብዬ (፪x)

ዛሬም አለሁኝ ተደላድዬ

ጠላት በእኔ ላይ በተነሳ ጊዜ

ነፍሴን ሊያስፈራራ ከቦኝ በትካዜ

ኢየሱስ ደረስህልኝ አሳርፈኽኛል

ስምህ ጋሻ ሆኖ አስመልጠኸኛል (፬x)

ዛሬ አድርሰኸኛል

አላፈርኩም አንተን ብዬ (፪x)

ዛሬም አለሁኝ ተደላድዬ

ድንቅ ታምራትህን ማዳንህን እያየሁ

ቃል ኪዳን አለብኝ አገለግላለሁ

ገና የሚበልጥ አዲስ ክብር አለ

ዛሬ ዓይኔ ከሚያየው ከዚህ የተሻለ (፬x)

ሌላ ክብር አለ

አላፈርኩም አንተን ብዬ (፪x)

ዛሬም አለሁኝ ተደላድዬ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ