Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ለምልሟል

Lemlemual

2007 · ትራክ 7 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ምድረ በዳዬ ለምልሟል (፪x)

ኢየሱስ ዋጋ ከፍሎልኛል

የዘላለም ኪዳን ገብቶልኛል

የማይሻር ኪዳን ገብቶልኛል

፩) በልቤ ሲገባ የየሱሴ ፍቅሩ

ሕይወቴ ተገዛ ጨከነ ለፍቅሩ

ዛሬ በደስታ በአደባባይ ቆሜ

ያድናል እላለሁ ደግሜ ደግሜ

ኢየሱስ ጠበቃ ሆኖልኛል

ከእንግዲህ የትኛው ያሰጋኛል

፪) ዛሬ ምን ይዋጠው ያክፉ ጠላቴ

በጌታ በኢየሱስ ሙሉ ነው ሕይወቴ

ምክንያትን ፈላልጐ ዙሪያዬን ቢዞረው

እኔ እንደው አልገኝ አጥሬ ኢየሱስ ነው

ኢየሱስ ጠበቃ ሆኖልኛል

ከእንግዲህ የትኛው ያሰጋኛል

፫) ሞትን ድል አድርጐ በተነሳው ጌታ

እኔስ ተፈወስኩኝ ከሃጥያት በሽታ

ዓለም ሰይጣን ሥጋ ዳግም ላያገኙኝ

በጌታ በኢየሱስ ከሞት አመለጥኩኝ

ኢየሱስ ጠበቃ ሆኖልኛል

ከእንግዲህ የትኛው ያሰጋኛል

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ