አይዞህ
Ayzoh
2007 · ትራክ 4 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
መውጣትህ መግባትህ በእግዚአብሔር እጅ ነው
ታዲያ የምትፈራው ምትሰጋው ምንድነው
የሚያሰጋህ ታዲያ የቱ ነው (፪x)
በሁሉም ላይ ጌታ የበላይ ነው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ዙሪያህ የከበበህ ሁኔታ የማይሆን ቢመስልህ
የምታየው ሁሉ ቢዘጋ ግራ ቢገባህም
የምትፈራው ነገር ላይወርስህ
አይዞህ ኢየሱስ አለልህ
አዝማች · Chorus
መውጣትህ መግባትህ በእግዚአብሔር እጅ ነው
ታዲያ የምትፈራው ምትሰጋው ምንድነው
የሚያሰጋህ ታዲያ የቱ ነው (፪x)
በሁሉም ላይ ጌታ የበላይ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰበሰብኩኝ ስትል ያያዝከው ከእጅህ ቢበተንም
ተስፋ ያረከው ሁሉ እርቆ አልያዝ ቢልህም
በእግዚአብሔር ሀሳብ ላይ ኑር እንጂ
አይዞህ አለህ ወዳጅ
አዝማች · Chorus
መውጣትህ መግባትህ በእግዚአብሔር እጅ ነው
ታዲያ የምትፈራው ምትሰጋው ምንድነው
የሚያሰጋህ ታዲያ የቱ ነው (፪x)
በሁሉም ላይ ጌታ የበላይ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አልጥልህም ብሎ የጠራህ እግዚአብሔር ታማኝ ነው
ላንተ ባይመስልህም አላማው ሁሉ ለበጐ ነው
ሳትፈራ ጥቂት ታገሰው
ጽና ማጉረምረሙን ተወው
አዝማች · Chorus
መውጣትህ መግባትህ በእግዚአብሔር እጅ ነው
ታዲያ የምትፈራው ምትሰጋው ምንድነው
የሚያሰጋህ ታዲያ የቱ ነው (፪x)
በሁሉም ላይ ጌታ የበላይ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ