Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ትልቅ

Teleq

2007 · ትራክ 3 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የዘለዓለም መኖሪያዬ

አንተ እኮ ነህ ማረፊያዬ

ታምኘብህ አላፈርኩም

በምድረበዳ አልቀረሁም

ትልቅ ያየሁት አንተን ብቻ

በምድር በሰማይ የለህ አቻ

እግዚአብሔር አንተ እግዚአብሔር ነህ

ከአማልክት ሁሉ ትለያለህ (፪x)

ካየሁት ሁሉ ትበልጣለህ

በክንዶችህ አየተደገፍኩ

አቤት ባንተ ስንቱን አለፍኩ

ማዳንህን አይቻለሁ

ስለውለታህ እዝምራለሁ

ትልቅ ያየሁት አንተን ብቻ

በምድር በሰማይ የለህ አቻ

እግዚአብሔር አንተ እግዚአብሔር ነህ

ከአማልክት ሁሉ ትለያለህ (፪x)

ካየሁት ሁሉ ትበልጣለህ

የዚህ ዓለም ጠቢባኖች

የምድር ላይ ኃያላኖች

ሁሉም ወድቀው ተረስተዋል

አንተ ብቻ ያው ነህ ተከብረሃል

ትልቅ ያየሁት አንተን ብቻ

በምድር በሰማይ የለህ አቻ

እግዚአብሔር አንተ እግዚአብሔር ነህ

ከአማልክት ሁሉ ትለያለህ (፪x)

ካየሁት ሁሉ ትበልጣለህ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ