አለኝ
Alegn
2007 · ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አለኝ እኔስ አለኝ ብዬ ምታመነው
ዘመን የማይሽረው ለእኔስ ኢየሱስ ነው
፩) ሁሉ ሙሉ ሆኖ እጥፍ ቢኖረንም
ለነፍሴ ጠበቃ ዋስ አይሆንልኝም
ለኔ አለኝ የምለው ሁሉ የማመልከው
አልፋማ ኦሜጋ ትልቅ ኢየሱስ ነው
አዝማች · Chorus
አለልኝ የምለው
ለእኔስ ኢየሱስ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
፪) ዝና ከበሬታ በዚህ በምድር ነው
አንድ ቀን ሲያበቃ ሁሉም አላፊ ነው
በሰማይ ቢሆን ደግሞም በምድር
ለኔስ ድጋፍ አለኝ የማይሰበር
አዝማች · Chorus
አለልኝ የምለው
ለእኔስ ኢየሱስ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
፫) ሰው ከማይገምተው ካልታሰበ ስፍራ
በፍቅሩ ማረከኝ ክብሩን እንዳወራ
ከሳሾቹን ሁሉ እያሳፈረልኝ
አዲስን ዝማሬ በአፌ ጨመረልኝ
አዝማች · Chorus
አለልኝ የምለው
ለእኔስ ኢየሱስ ነው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
፬) ለሰይጣን ሽንገላ ጆሮዬን አልሰጥም
ቢያወራ ቢያወራ ተስፋዬን አልጥልም
ቢጐድልም ቢሞላ ጌታን አመልካለሁ
ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ እርሱን እግኝቻለሁ
አዝማች · Chorus
አለልኝ የምለው
ለእኔስ ኢየሱስ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ