ነፍሴ ሆይ
Nefsie Hoy
2007 · ትራክ 10 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ነፍሴ ሆይ ዘምሪ ለወደደሽ ጌታ
አንቺን ከገሃነም ከሲኦል ላወጣ
እስኪ ድምጽሽን አሰሚ
ኢየሱስ ያድናል እያልሽ ዘምሪ
ቁጥር 1 · Verse 1
፩) ኢየሱስ በፍቅሩ ወዶሻል
ሞትን ድል አድርጐ ከአብ አስታርቆሻል
ታዲያ ለምን እረሳሽው ይህንን ውለታ
ዘምሪለት እንጂ ከጥዋት እስከ ማታ
አዝማች · Chorus
ነፍሴ ሆይ ዘምሪ ለወደደሽ ጌታ
አንቺን ከገሃነም ከሲኦል ላወጣ
እስኪ ድምጽሽን አሰሚ
ኢየሱስ ያድናል እያልሽ ዘምሪ
ቁጥር 2 · Verse 2
፪) ሞትና መውጊያውን ሰባብሮ
አንችን ግን መርጦሻል ጠላትን አባሮ
አትቆጥቢ ተናገሪ የምስራቹን ቃል
ላመኑት ሁሉ መጠጊያ ይሆናል
አዝማች · Chorus
ነፍሴ ሆይ ዘምሪ ለወደደሽ ጌታ
አንቺን ከገሃነም ከሲኦል ላወጣ
እስኪ ድምጽሽን አሰሚ
ኢየሱስ ያድናል እያልሽ ዘምሪ
ቁጥር 3 · Verse 3
፫) ነፍሴ ሆይ በእግዚአብሔር ታመኚ
ባለውለታሽን እርሱን አመስግኝ
ምህረቱ ለዘላለም አቁሞሻልና
ማዳኑ ይነገር ዛሬም እንደገና
አዝማች · Chorus
ነፍሴ ሆይ ዘምሪ ለወደደሽ ጌታ
አንቺን ከገሃነም ከሲኦል ላወጣ
እስኪ ድምጽሽን አሰሚ
ኢየሱስ ያድናል እያልሽ ዘምሪ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ