ቃል ተናገር
Qal Tenager
2007 · ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አንተ ይሁን ስትል የማይሆን ምን አለ (፪x)
ቃል ተናገር እንጂ የማይሆን ምን አለ (፪x)
ጊዜ የማይሽረው ባለበት የሚገኝ
እንዳንተ አላይሁም እንደቃሉ ታማኝ
ቁጥር 1 · Verse 1
፩) አቤት የእኔ ጌታ ስራህ ያስገርማል
ሰማይና ምድርን በቃልህ ሰርተሃል
በመገዛት ያድራል ፍጥረት በሥልጣንህ
ታስተዳድራለህ የለም የሚያቅትህ
አዝማች · Chorus
አንተ ይሁን ስትል የማይሆን ምን አለ (፪x)
ቃል ተናገር እንጂ የማይሆን ምን አለ (፪x)
ጊዜ የማይሽረው ባለበት የሚገኝ
እንዳንተ አላይሁም እንደቃሉ ታማኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
፪) ይሁን ያልከው ሁሉ መፈጸሙ ላይቀር
የሰው ላይ ታች ማለት ምንድነው መሸበር
እኔስ ለፈቃድህ ራሴን ሰጥቻለሁ
አንተ ያልከው ይሁን እገዛልሃለሁ
አዝማች · Chorus
አንተ ይሁን ስትል የማይሆን ምን አለ (፪x)
ቃል ተናገር እንጂ የማይሆን ምን አለ (፪x)
ጊዜ የማይሽረው ባለበት የሚገኝ
እንዳንተ አላይሁም እንደቃሉ ታማኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
፫) ምንም በሌለበት በምድረበዳው
ታማኝነትህን አይቻለሁ
ዛሬም ክንደ ብርቱ ገናና ነህና
ያልከው ሁሉ ይሆናል ሀይል ያንተ ነውና
አዝማች · Chorus
አንተ ይሁን ስትል የማይሆን ምን አለ (፪x)
ቃል ተናገር እንጂ የማይሆን ምን አለ (፪x)
ጊዜ የማይሽረው ባለበት የሚገኝ
እንዳንተ አላይሁም እንደቃሉ ታማኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ