አላይም የኋላ
Alayem Yehuala
2007 · ትራክ 9 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር አዋቂ ነው (፪x)
ያለውን ሊፈጽም ለሁሉም ጊዜ አለው
ለአንተም ጊዜ አለው ለአንቺም ጊዜ አለው
ለእኔም ጊዜ አለው ለሁሉም ጊዜ አለው
ቁጥር 1 · Verse 1
፩) በሰማይ የሚታይ ደመና ባይኖርም
ንፋስም ባይኖርም አይዘንብም አልልም
የተናገረኝን አልጠረጥረውም (፪x)
እርሱ ይሆናል ካለ አይሆንም አልልም
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር አዋቂ ነው (፪x)
ያለውን ሊፈጽም ለሁሉም ጊዜ አለው
ለአንተም ጊዜ አለው ለአንቺም ጊዜ አለው
ለእኔም ጊዜ አለው ለሁሉም ጊዜ አለው
ቁጥር 2 · Verse 2
፪) አላሳልፍ ብሎ ዮርዳኖስ ቢሞላ
ጉልበቴን ሊያላላ አላይም የኋላ
የጠራኝን አምላክ ቃሉን አምነዋለሁ እታመነዋለሁ
በእምነት ተሻግሬ በድል እቆማለሁ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር አዋቂ ነው (፪x)
ያለውን ሊፈጽም ለሁሉም ጊዜ አለው
ለአንተም ጊዜ አለው ለአንቺም ጊዜ አለው
ለእኔም ጊዜ አለው ለሁሉም ጊዜ አለው
ቁጥር 3 · Verse 3
፫) በጉልበቱ ጽናት የሚራመደው (፪x)
አምላኬ እርሱ ነው
ከፍ ከፍ ቢያደርግ ሲያሻው ቢከለክል (፪x)
በሚሰራው ሁሉ እግዚአብሔር ትክክል (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር አዋቂ ነው (፪x)
ያለውን ሊፈጽም ለሁሉም ጊዜ አለው
ለአንተም ጊዜ አለው ለአንቺም ጊዜ አለው
ለእኔም ጊዜ አለው ለሁሉም ጊዜ አለው
ቁጥር 4 · Verse 4
፬) አምላክህ ትቶሃል ጠላቴ ቢለኝም
ቢነዘንዘኝም ይህ ለኔ አይገባኝም
ምንም ቀን ቢገፋ ተስፋው ቢዘገይም
አምላኬ ያለው ቃል መፈጸሙ አይቀርም
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር አዋቂ ነው (፪x)
ያለውን ሊፈጽም ለሁሉም ጊዜ አለው
ለአንተም ጊዜ አለው ለአንቺም ጊዜ አለው
ለእኔም ጊዜ አለው ለሁሉም ጊዜ አለው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ