Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተማምኜ

Temamegnie

2007 · ትራክ 5 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ላመስግን የኔጌታ ላመስግን

ላመስግን ደጋግሜ ላመስግን

በጠላቴ ሰፍር እሮሮ ሲሰማ

ለእኔ ግን በዛልኝ የምሥጋና ዜማ

ከፊቴ የቆመው ትልቁ ተራራ

ደልዳላ ሆነልኝ ስምህን ስጠራ

ከፊቴ የቆመው ትልቁ ተራራ

ደልዳላ ሆነልኝ ስምህን ስጠራ

ተማምኜ እኖራለሁ ተማምኜ (፪x)

በዘላለሙ ክንድህ በቅፍህ ታምኜ

አልጥልህም ብለህ በፍቅርህ ጠርተኽኝ ፀጋን አለበስከኝ

በሄድኩበት ሁሉ ተከናወነልኝ ሞገስ ሆነህልኝ

እንድም ነገር የለም ከኔ ነው የምለው የኔ ነው የምለው

ሁሉም ያማረልኝ ኢየሱስ ባንተ ነው ጌታዬ ባንተ ነው

ተማምኜ እኖራለሁ ተማምኜ (፪x)

በዘላለሙ ክንድህ በቅፍህ ታምኜ

ውድቀቴን በሚሻው በጠላቴ ላይ (፪x)

ከፍ ከፍ አረከኝ ክብርህ እንዲታይ (፪x)

ልቤ በማዳንህ እየተደነቀ (፪x)

ለታላቅነትህ ዜማን አፈለቀ (፪x)

ተማምኜ እኖራለሁ ተማምኜ (፪x)

በዘላለሙ ክንድህ በቅፍህ ታምኜ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ