Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አልባሽ አርገኝ

Albash Adegeg

ትራክ 2 · 5:24 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የወንድሞቼ የእህቶቼን

እራቁት አልባሽ አርገኝ እግዚአብሔር

የካም መንፈስ ይራቅ ከእኔ

እልባሽ አርገኝ ለወገኔ (፪x)

ኖህን ልጁ አዋረደው

አንድ ቀን ድንገት ሰክሮ ቢያየው [1]

ምን አለበት ልብስ ቢያለብሰው

ይህ ቀን አልፎ እኮ ይሆናል ሰው

የወንድሞቼን የእህቶቼን

ገመና ሸፋኝ አርገኝ እግዚአብሔር

የካም መንፈስ ይራቅ ከእኔ

አልባሽ አርገኝ ለወገኔ

ብዙ . (1) . ለብሰዋል

የንስሃ ጊዜ እጥተዋል

ራቁትነትን አልባሽ ጠፍቶ

ቀረ የትም ህዝብህ ወጥቶ

የወንድሞቼን የእህቶቼን

እራቁት አልባሽ አርገኝ እግዚአብሔር

የካም መንፈስ ይራቅ ከእኔ

አልባሽ አርገኝ ለወገኔ

ድካም መግለጥ የወንድምን

መሰብሰብ ነው ራስ መርገምን

አይጠቅመንም ለእኔም ለእርሱም

ይልቅ ይበጃል ልብስ ማልበሱ

የወንድሞቼን የእህቶቼን

ገመና ሸፋኝ አርገኝ እግዚአብሔር

የካም መንፈስ ይራቅ ከእኔ

አልባሽ አርገኝ ለወገኔ

ለወንድሜ ጥቃት ደራሽ

እራቁትነቱን አልባሽ

የደከመን ማበረታ

ምርጫዬ ነው ልሁን ጌታ

የወንድሞቼን የእህቶቼን

ገመና ሸፋኝ አርገኝ እግዚአብሔር

የካም መንፈስ ይራቅ ከእኔ

አልባሽ አርገኝ ለወገኔ

የአባታቸውን ሀፍረት ማየት

አልውደዱም ሴምና ያፌት

ሸማ አምጥተው አለበሱት

ቀን መጣለት በረታ አሱም [2]

የወንድሞቼን የእህቶቼን

ድካም አጋዥ አርገኝ እግዚአብሔር

የካም መንፈስ ይራቅ ከእኔ

አልባሽ አርገኝ ለወገኔ (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ