ማራናታ
Maranatha
ትራክ 9 · 6:00 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ለአንተ የሚሳንህ መቼም የለምና
የድንጋይ ልብን የሥጋ አድርግና
በምህረት ዓይንህ ተመልከተንና
ከዚህ ዓለም አላቀን ኢየሱስ ቶሎ ና
ማራናታ ጌታ ቶሎ ና
ቁጥር 1 · Verse 1
ከዚህ ዓለም አላቀን ኢየሱስ ቶሎ ና
ማራናታ ጌታ ቶሎ ና (፪x)
ስለኃጢአቱ የሞትክለት ህዝብ
በዚህ ዓለም ገዚ ልቡ ተያዘልህ
አንተ በቀጭኑ መንገድ ኑ ትላለህ
ህዝብህ ግን በሰፊው ገብቶ አለቀልህ
መልሰው ጌታ ቶሎ ናለት
አዝማች · Chorus
ለአንተ የሚሳንህ መቼም የለምና
የድንጋይ ልብን የሥጋ አድርግና
በምህረት ዓይንህ ተመልከተንና
ከዚህ ዓለም አላቀን ኢየሱስ ቶሎ ና
ማራናታ ጌታ ቶሎ ና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ክብርህን በመተው እራህን አዋርደህ
ሥጋ በመልበስ በምድር ተንከራተህ
የሞትክለት ህዝብህ ኃይሉ ትጨፍኗል
ማስተዋሉ ጠፍቶ ልቡ ተተብትቧል
ጐብኚ አንተ ነህና ኢየሱስ ጐብኘን ይላል
አዝማች · Chorus
ለአንተ የሚሳንህ መቼም የለምና
የድንጋይ ልብን የሥጋ አድርግና
በምህረት ዓይንህ ተመልከተንና
ከዚህ ዓለም አላቀን ኢየሱስ ቶሎ ና
ማራናታ ጌታ ቶሎ ና (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ለአባቶቻችን እንደረዳሃቻው
ከግብጽ ባርነት እንዳወጣሃቸው
እንዳወረስካቻው የተስፋውን ቦታ
እኛም ከዚህ ዓለም ገዢም ሥር
እንፈታ ጐብኘን ጌታ
አዝማች · Chorus
ለአንተ የሚሳንህ መቼም የለምና
የድንጋይ ልብን የሥጋ አድርግና
በምህረት ዓይንህ ተመልከተንና
ከዚህ ዓለም አላቀን ኢየሱስ ቶሎ ና
ማራናታ ጌታ ቶሎ ና (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከአንበሶች ጉድጓድ የሚያወጣው ኃይልህ
ከእሳት ነበልባል የሚያወጣው ክንድህ
ዛሬም በእኛ ዘመን እባክህ ይዘርጋ
ህዝብህን አድነው ከሰይጣን መንጋጋ
እኛን እርዳን እንድንተጋ
አዝማች · Chorus
ለአንተ የሚሳንህ መቼም የለምና
የድንጋይ ልብን የሥጋ አድርግና
በምህረት ዓይንህ ተመልከተንና
ከዚህ ዓለም አላቀን ኢየሱስ ቶሎ ና
ማራናታ ጌታ ቶሎ ና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ