ኢየሱስ ነው ምርጫዬ
Eyesus New Merchayie
ትራክ 7 · 5:18 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ለእኔስ አዳኜ
ኢየሱስ ነው ምርጫዬ
የልብ ወዳጄ የእውነት የእውነት
የእውነት አፍቃሪዬ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እናት ልጇን በጣር ትወልዳለች
ወልዳ ጡት አጥብታ ታሳድጋለች
በነፍሷ ላይ ድንገት ችግር ሲመጣ
ወንዝ ውስጥ ጣለችው ሙሴን አውጥታ
ግን አምላኩ እግዚአብሔር ሰበሰበው
በንጉሡ ቤት በተዓምር አሳደገው [1]
ለሞት የተሰጠውን አነሳና
በህዝቡ ላይ ሾመው ፀጋ አበዛና [2]
አዝማች · Chorus
ለእኔስ አዳኜ
ኢየሱስ ነው ምርጫዬ
የልብ ወዳጄ የእውነት የእውነት
የእውነት አፍቃሪዬ
ቁጥር 2 · Verse 2
አጋር በምድረ በዳ ተሰደደች
አባት በልጁ ሲጨክን አየች
ውኃም አለቀ ምንዎን ታጠጣው
ጨነቃትና እራቀች ጥላው
ግን እግዚአብሔር ፈጥኖ መጣላት
ውሃውን አየች ዓይኗን ከፍቶላት
የሚያያትንም አየችውና
ቤቷ መለሳት ተስፋ ሰጣትና [3]
አዝማች · Chorus
ለእኔስ አዳኜ
ኢየሱስ ነው ምርጫዬ
የልብ ወዳጄ የእውነት የእውነት
የእውነት አፍቃሪዬ
ቁጥር 3 · Verse 3
ወንድምንም አየሁት ጉድጓድ ሲጥል
ለባርነትም ሲሸጥ ለባዕድ ወገን [4]
ጌታ ግን ከግዞት አወጣውና
በረከት ሆነ ዮሴፍ ነገሠና [5]
ከሞተ አራት ቀን ሆኖታል
አለችው እህቱ አሁንስ ሸቶአል
የኢየሱሴ ፍቅር መቸ ያሸተዋል
አላዛርን በድንቅ ከሞት ያስነሳዋል [6]
አዝማች · Chorus
ለእኔስ አዳኜ
ኢየሱስ ነው ምርጫዬ
የልብ ወዳጄ የእውነት የእውነት
የእውነት አፍቃሪዬ
ቁጥር 4 · Verse 4
እዮብ በቁስል እጅግ ተመቶ
ሚስቱ እንኳን ጠልታው የሚቀርበው አጥቶ
ክደህ ሙት ብላ ስታስቸግረው
በሸክሙ ላይ ቀንበር ስትጭነው [7]
አምላኩ እግዚአብሔር ከተፍ አለለት
ምርኮውን በእጥፍ በእጥፍ መለሰለት [8]
ሁሉንም በተራው አየሁት ቃኘሁት
ግን ኢየሱሴን በልጦ አገኘሁት
አዝማች · Chorus
ለእኔስ አዳኜ
ኢየሱስ ነው ምርጫዬ
የልብ ወዳጄ የእውነት የእውነት
የእውነት አፍቃሪዬ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ