Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ለበጐ ነው

Lebego New

ትራክ 8 · 8:04 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እግዚአብሔርን ለሚወዱት

እንድ ሃሳቡም ለተጠሩ

ነገር ሁሉ ለበጐ እንዲደረግ እናውቃለን

ስለዚህ ጌታን (፫x)

እናመሰግናለን (፪x)

እርሱ አይሳሳትም ሁልጊዜ ልክ ነው

ደግሞም የሚሆነው ሁሉ ለበጐ ነው

የእኛ ሃሳብ ካልሆነ ይቅር ምሬታችን

የያዝነውን ጌታ መጠራጠራችን (፪x)

እግዚአብሔርን ለሚወዱት

እንድ ሃሳቡም ለተጠሩ

ነገር ሁሉ ለበጐ እንዲደረግ እናውቃለን

ስለዚህ ጌታን (፫x)

እናመሰግናለን

የፀሎት መልስ ቢዘገይ ቢሆንም ዝምታ

ብዙ ጥያቄዬ እንኳን መልስ ቢያጣ

የጠራኝ ታማኝ ነው እኔስ አምነዋለሁ

ስንቱን አሳልፎኝ እዚህ ደርሻለሁ (፪x)

እግዚአብሔርን ለሚወዱት

እንድ ሃሳቡም ለተጠሩ

ነገር ሁሉ ለበጐ እንዲደረግ እናውቃለን

ስለዚህ ጌታን (፫x)

እናመሰግናለን

በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል

ጌታውን የሚጠብቅ ደግሞ ይከብራል

ብዙ አድርጐልኛል እመሰክራለሁ

እናንተም እመኑት ደግሜ እላለሁ (፪x)

እግዚአብሔርን ለሚወዱት

እንድ ሃሳቡም ለተጠሩት

ነገር ሁሉ ለበጐ እንዲደረግ እናውቃለን

ስለዚህ ጌታን (፫x)

እናመሰግናለን

የሚያልፍ ባይመስልም በዝቶ ችግራችን

የራቀ ቢመስልም ጌታ ከጐናችን

ቆመን እንጠብቀው በመጠበቂያችን

ተስፋውን የሰጠን ታማኝ ነው ጌታችን (፪x)

እግዚአብሔርን ለሚወዱት

እንድ ሃሳቡም ለተጠሩት

ነገር ሁሉ ለበጐ እንዲደረግ እናውቃለን

ስለዚህ ጌታን (፫x)

እናመሰግናለን

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ