Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ክበር መድሃኒቴ

Keber Medhanitie

ትራክ 4 · 6:28 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ስዝል ሲያቅተኝ ስደክም

ጌታዬ አንተ አልተውከኝም

ድምፅህ መጣ ለሕይወቴ

በረታ ቁርጭምጭሚቴ ክበር መድሃኒቴ (፪x)

ልባችን ሲዝል ሲደነድን

አለህ ማድቀቁያ መዶሻ ቃል

ለደረቀ አጥንት ሕይወት ይሰጣል

ታላቅ ሰራዊት አርጐ ያቆማል

ስዝል ሲያቅተኝ ስደክም

ጌታዬ አንተ አልተውከኝም

ድምጽህ መጣ ለሕይወቴ

በረታ ቁርጭምጭሚቴ ክበር መድሃኒቴ

ዛፍ ስር ስንወድቅ አይሎ ሰልፍ

የስንፍናን ቃል ስንለፈልፍ

ትከሻህ አይዝል ፊትህ አይጠቁርም

የወደድከውን ሰውን አትጥልም

ስዝል ሲያቅተኝ ስደክም

ኢየሱስ አንተ አልተውከኝም

ቃልህ መጣ ለሕይወቴ

በረታ ቁርጭምጭሚቴ ክበር መድሃኒቴ

ቃልህ ጅማትን ቅልጥም ይወጋል

ነፍስንና መንፈስንም ይለያል

በምክሩም ግሩም ጣፋች ሲበላ

እንከን የሌለው የማር ወለላ

ስዝል ሲያቅተኝ ስደክም

ጌታያ አንተ አልተውከኝም

ድምጽህ መጣ ለሕይወቴ

በረታ ቁርጭምጭሚቴ ክበር መድሃኒቴ

ኢየሱስ በቃሉ የፈወሳችሁ

በቅዱስ መንፈሱ የነካካችሁ

እንደኔ ደስ ደስ ደስ ያላችሁ

አክብሩት ጌታን እልል ብላችሁ

ስዝል ሲያቅተኝ ስደክም

ጌታዬ አንተ አልተውከኝም

ድምጽህ መጣ ለሕይወቴ

በረታ ቁርጭምጭሚቴ ክበር መድሃኒቴ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ