ኢየሱስ ትክክል
Eyesus Tekekel
ትራክ 1 · 5:25 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ቢመች ባይመች ቢሞላ ቢጐድልም
ቁጥር 1 · Verse 1
ብትሰጥ ብትከለክል ብትገል ብታድን
ሥም አወጣሁልህ ብዬ ትክክል
አሜን ጌታ ትክክል (፪x)
የበጐቹ መብዛት የላሞች መርባት
የርሻው መብልን መስጠት ጐተራው መሙላት
ሁሉም ተስብስቦ ቢከብ በዙሪያዬ
የሚያህልህ የለም ኢየሱስ ጌታዬ
ቁጥር 2 · Verse 2
ቢመች ባይመች ቢሞላ ቢጐድል
ቁጥር 3 · Verse 3
ብትሰጥ ብትከለክል ብትገል ብታድን
ሥም አወጣሁልህ ብዬ ትክክል
አሜን ጌታ ትክክል
መለኪያዬ ችግር እይደለም ማጣት
ወይ አግኝቶ መክበር ምድራዊ ሃብት
ለእኔ ሚበጀውን ከአንተ ይልቅ ማን ያውቃል
ነፍስን ከመስጠት ሁሉስ መች ይበልጣል
አዝማች · Chorus
ቢመች ባይመች ቢሞላ ቢጐድልም
ቁጥር 4 · Verse 4
ብትሰጥ ብትከለክል ብትገል ብታድን
ሥም አወጣሁልህ ብዬ ትክክል
አሜን ጌታ ትክክል
ብሩንና ወርቁን ዓለምስ መች አታ
እርካታ አጣች እንጂ ሰጭውን እረስታ
ኢየሱሴ ለእኔ የሕይወቴ ጌታ
ቢሞላ ቢጐድል ሆንክልኝ ደስታ
አዝማች · Chorus
ቢመች ባይመች ቢሞላ ቢጐድልም
ቁጥር 5 · Verse 5
ብትሰጥ ብትከለክል ብትገል ብታድን
ሥም አወጣሁልህ ብዬ ትክክል
አሜን ጌታ ትክክል
የጸሎቴ መልሱ ቢዘገይም ፈውሴ
አንተ ካየህልኝ ተስማማሁ ኢየሱሴ
በጨለማው ስልጣን ጭንቅላት ላይ ቁሜ
እባርክሃለሁ ደግሜ ደግሜ
አዝማች · Chorus
ቢመች ባይመች ቢሞላ ቢጐድልም
ቁጥር 6 · Verse 6
ብትሰጥ ብትከለክል ብትገድል ብታድን
ሥም አወጣሁልህ ብዬ ትክክል
አሜን ጌታ ትክክል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ