ክበር ተመስገን
Keber Temesgen
ትራክ 5 · 4:17 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዐይኔ በማየቱ አንተን ያደንቅሃል
ጆሮዬ በመስማቱ ከፍ ያደርግሃል
ነፍስ መንፈስ ሥጋዬ አንተን ሾመውሃል
ተስማምተው ኢየሱስ ይግዛን ብለውሃል
አዝማች · Chorus
ክበር ተመስገን ክበር (፪x) እግዚአብሔር
ቁጥር 2 · Verse 2
ክበር ተመስገን ንገሥ (፪x) ጌታ እየሱስ
አበቦች ፈንድቁ እንሰሶች ዝለሉ
ዛፎች አሸብሽቡ አእዋፍ ዘምሩ
አዲስ ምሥጋና አምጡ አሜን ዕልል በሉ
በፊቱ ስገዱ ፍጥረታት በሙሉ
አዝማች · Chorus
ክበር ተመስገን ክበር (፪x) እግዚአብሔር
ቁጥር 3 · Verse 3
ክበር ተመስገን ክበር ንገሥ መስፈስ ቅዱስ
ከበሮው ይመታ በገናው ይደርደር
መለከት ይነፋ እምቢልታው ይጨመር
ክራሩንም ቃኙት አዲስ ቅኔ መዝሙር
በእግዚአብሔር ምሥጋና ይሙላ ሰማይ ምድር
አዝማች · Chorus
ክበር ተመስገን ክበር (፪x) እግዚአብሔር
ቁጥር 4 · Verse 4
ክበር ተመስገን ንገሥ ጌታ ኢየሱስ
ፏፏቴዎች ፈንጩ በአምላካችሁ ፊት
ጨረቃ ድመቂ ፍኩ ከዋክብት
ብቻውን ታምራት ድንቅ አድርጓልና
ዙፋኑን ይክበበው ክብርና ምሥጋና
አዝማች · Chorus
ክበር ተመስገን ክበር (፪x) እግዚአብሔር
ቁጥር 5 · Verse 5
ክበር ተመስገን ንገሥ ጌታ ኢየሱስ
ክበር ተመስገን ንገሥ መንፈስ ቅዱስ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ