ልበል እንደ ማሪያም
Lebel Ende Mariyam
ትራክ 6 · 7:18 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ልበል እንደ ማርያም ሚላችሁን አርጉ
ቁጥር 1 · Verse 1
እርሱ ኤልሻዳይ ነው አንዳች እንዳትሰጉ
አንድ ነገር ብቻ አሃሃ አውቃለሁ ገብቶኛል
ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ካለ እሰይ ይበቃኛል (፪x)
ሰዎች ሰርግ ደግሰው እጅግ በሰፊው
የወይን ጠጁ አልቆ ጉድ አረጋቸው
ሲወጡ ሲገቡ ተጨንቀው እያለ
የናዝሬቱ ኢየሱስ አሃሃ ለካስ እዚያ ቤት አለ
ኢየሱስ ጣልቃ ገባ ዲያብሎስ ከሰረ
ውሃው ግሩም ጣዕም ያለው ወይን ጠጅ ሆነ
አዝማች · Chorus
ልበል እንደ ማርያም ሚላችሁን አርጉ
ቁጥር 2 · Verse 2
እርሱ ኤልሻዳይ ነው አሜን አንዳች እንዳትሰጉ
አንድ ነገር ብቻ አሃሃ አውቃለሁ ገብቶኛል
ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ካለ አሜን ይበቃኛል
ወገኖች እኛንም ችግር ሲገጥመን
እንበለው እንደዚህ ጌታ ኢየሱስን
ኢየሱሴ ግባ በቤቴ ታደም
ኑሮዬ ያለአንተ አሃሃ ትርጉም የለውም
ብቻ ይሁን እንጂ እርሱ ከእኛ ጋራ
ደልዳላ ይሆናል ትልቁ ተራራ
አዝማች · Chorus
ልበል እንደ ማርያም ሚላችሁን አርጉ
ቁጥር 3 · Verse 3
እርሱ ኤልሻዳይ ነው አሜን አንዳች እንዳትሰጉ
አንድ ነገር ብቻ አሃሃ አውቃለሁ ገብቶኛል
ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ካለ አሜን ይበቃኛል
የኢየሱስ ወዳጅ ድንገት ታመመና
ወደ ኢየሱስ ላኩ ብለው በቶሎ ና
ጌታም አልፈጠነ አሃሃ አለአዛርም ሞተ
አራት ቀን ሆነው ተቀብሮ ሸተተ
ቢዘገይም እንኳን ጌታ ኢየሱስ መጣ
የሞተው ከቀብሩ ሕያው ሆኖ ወጣ
አዝማች · Chorus
ልበል እንደ ማርያም ሚላችሁን አርጉ
ቁጥር 4 · Verse 4
እርሱ ኤልሻዳይ ነው አሜን አንዳች እንዳትሰጉ
አንድ ነገር ብቻ አሃሃ አውቃለሁ ገብቶኛል
ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ካለ ይሁን ይበቃኛል
ዝናቡ ፀሃዯ ነፋሱ አየሩ
እንዳስፈለጋችሁ ብትቀያየሩ
ጌታ ከእኔ ጋራ ነው ምንድን ያስፈራኛል
ቁራን እየላከ ቢያስፈልግ ጮማን ያበላኛል
ስደክም ኃይል ሰጥቶ ስወደቅ አንስቶ
ቤቱ ያደርሰኛል ሃያል ክንዱ መርቶ
አዝማች · Chorus
ልበል እንደ ማርያም ሚላችሁን አርጉ
ቁጥር 5 · Verse 5
እርሱ ኤልሻዳይ ነው አሜን አንዳች እንዳትሰጉ
አንድ ነገር ብቻ አሃሃ አውቃለሁ ገብቶኛል
ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ካለ እሰይ ይበቃኛል (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ