Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሃገሬን አስባት

Hagerien Asebat

ትራክ 3 · 8:58 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኦ ሃገሬን አስባት ኢትዮጵያን አስባት

የተዘጋውን ደጅ ከፍተህ ጌታ/ኢየሱስ

ሰላም ለአንቺ ይሁን በላት (፪x)

እግዚአብሔር አስባት ጐብኛት ኢትዮጵያን

እማጸንሃለሁ ጌታ ሆይ አፍስሼ እንባዬን

እግዜአብሄር ነህ ለኛ መድህኒታችን

ስለ ሥምህ አስብ አባት ሆይ የተስፋ ቃልህን

ኦ ሃገሬን አስባት ኢትዮጵያን አስባት

የተዘጋውን ደጅ ከፍተህ ጌታ

ሰላም ለአንቺ ይሁን በላት (፪x)

ለልጅ ልጅ የሚተርፍ ቢኖር የአባት በደል

መሃሪ ነህና ጌታ ሆይ እባክህ ይቅር በል

መቅሰፍት ጉስቁልና ከእንግዲህስ ያብቃ

ከዙፋንህ ተነስ ጌታ ሆይ አንተ ግባ ጣልቃ

ኦ ሃገሬን አስባት ኢትዮጵያን አስባት

የተዘጋውን ደጅ ከፍተህ ኢየሱስ

ሰላም ለአንቺ ይሁን በላት

እጁዋን አንስታለች ወደ አንተ ከፍ አድርጋ

መፍትሄ ሚገኘው ጌታ ሆይ ነውና ከአንተ ጋ

ወንዶችና ሴቶች ትልቅ ትንሾችም

እንለምንሃለን ጌታ ሆይ ወድቀን በእግርህ ታች

ኦ ሃገሬን አስባት ኢትዮጵያን አስባት

የተዘጋውን ደጅ ከፍተህ ጌታ

ሰላም ለአንቺ ይሁን በላት

ለምድራችን ከአንተ ፍቅር ሰላም ይምጣ

በዲያቢሎስም ላይ ጌታ ሆይ ተነሳ በቁጣ

ሰማይ ይከፈት በረከትህ ይምጣ

የተጠማው ህዝብህ ጌታ ሆይ ጠጥቶ እንዲረካ

ኦ ሃገሬን አስባት ኢትዮጵያን አስባት

የተዘጋውን ደጅ ከፍተህ ጌታ/ኢየሱስ

ሰላም ለአንቺ ይሁን በላት (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ