አለብኝ ትዝታ
Alebegn Tezeta
ትራክ 2 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እኔ የማይረሳኝ ውለታ
አለብኝ አንድ ትዝታ
ቀራንዮ መስቀሉ ላይ
ሞቶ ያዳነኝ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔን ለማዳን ነው የደም ላብ ያላበህ የሞትክልኝ
ተሰቃየህልኝ መርገሜን ወሰድከው ልታድነኝ
ልጅህ ነኝ በጣር የወለድከኝ ሕይወትና ሰላም የሆንከኝ
በሞትህ እኔን ስታድነኝ አየሁ የመስቀሉ ፍቅርህን
(አልረሳውም እኔ) ለኔ የዋልክልኝ አለብኝ ውለታ
(አልረሳውም እኔ) ተሰቃየህልኝ ሞትክልኝ ጎልጎታ
(አልረሳውም እኔ) ዘመኔን በሙሉ አንተን ባመልክህ
(አልረሳውም እኔ) ምክንያቴ ይሄ ነው የመስቀል ፍቅርህ
አዝማች · Chorus
እኔ የማይረሳኝ ውለታ
አለብኝ አንድ ትዝታ
ቀራንዮ መስቀሉ ላይ
ሞቶ ያዳነኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አምላክ ሆነህ ሳለህ ሲያንገላቱህና ሲያፌዙብህ
እንደወንጀለኛ አስረው ሲገርፉህስ መች ራሩልህ
ሲንቁህ ሲሳበቁብህ ፥ መልስም አልነበረህ ሲወግሩህ
ለኔ ነው ይህ ሁሉ የሆነው ፥ እንዴት እንድትወደኝ እንዳየው
(አልረሳውም እኔ) ለኔ የዋልክልኝ አለብኝ ውለታ
(አልረሳውም እኔ) ተሰቃየህልኝ ሞትክልኝ ጎልጎታ
(አልረሳውም እኔ) ዘመኔን በሙሉ አንተን ባመልክህ
(አልረሳውም እኔ) ምክንያቴ ይሄ ነው የመስቀል ፍቅርህ
ለኔ ነው ለኔ
በመስቀል ላይ የሞተው ስለኔ (፭x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ