Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አልተውም ማመስገን

Altewem Mamesgen

ትራክ 12 · 5:51 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አገኘሁኝ ብዬ አልፈነድቅም

አጣሁኝም ብዬ አምልኮ አልተውም

መዳኔ ይበቃኛል ለምሥጋና

የእግዚአብሔር ልጅነት አለኝና (፪x)

የደህንነቴ ነገር ከሞት መዳኔ

ጌታዬን ለማመስገን በቂ ነው ለእኔ

ጠላቴ ሆይ እፈር እላማርር

ብሞትም ያድነኛል እግዚእብሔር

(አልተውም) ጌታዬን ማመስገን

(አልተውም) ወጀቡ ቢበዛ

(አልተውም) እንደውም ልጨምር

(አልተውም) ምሥጋናዬን ላብዛ (፪x)

ለእኔ (ሁልጊዜ ማመስገኔ ምክንያቴ ነው መዳኔ)

ሁሌ (ሁልጊዜ ማመስገኔ ምክንያቴ ነው መዳኔ) (፪x)

አገኘሁኝ ብዬ አልፈነድቅም

አጣሁኝም ብዬ አምልኮ አልተውም

መዳኔ ይበቃኛል ለምሥጋና

የእግዚአብሔር ልጅነት አለኝና (፪x)

ዛሬ በበረከቱ ቢባርከኝ

የሰጠኝን መልሶ ቢወስድብኝ

እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ

ሥሙ ይባረክልኝ አምልኮ ላብዛ

(አልተውም) ጌታዬን ማመስገን

(አልተውም) ወጀቡ ቢበዛ

(አልተውም) እንደውም ልጨምር

(አልተውም) ምሥጋናዬን ላብዛ (፪x)

ለእኔ (ሁልጊዜ ማመስገኔ ምክንያቴ ነው መዳኔ)

ሁሌ (ሁልጊዜ ማመስገኔ ምክንያቴ ነው መዳኔ) (፪x)

በላይ በሰማይ ቤት አለ የሚሉ

ደስ ይበላቸው እልል ይበሉ (፪x)

ደስታዬ (ነው መዳኔ)

እረፍቴ (ነው መዳኔ)

ሰላሜ (ነው መዳኔ)

መዳኔ (ነው መዳኔ) (፪x)

በላይ በሰማይ ቤት አለ የሚሉ

ደስ ይበላቸው እልል ይበሉ (፪x)

ደስታዬ (ነው መዳኔ)

እረፍቴ (ነው መዳኔ)

ሰላሜ (ነው መዳኔ)

መዳኔ (ነው መዳኔ) (፪x)

ሰላሜ (ነው መዳኔ) መዳኔ (ነው መዳኔ) (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ