መኖር አልችልም
Menor Alchelem
ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሁልጊዜ ምናፍቅህ
የነፍሴ ጥማት የምትወድህ
ልዑል ነህ ለእኔ
እርሱ ነው ረሃቤ
ያለ አንተ መኖር አልችልም
ታውቃለህ አቅም እኔ የለኝም
ኢየሱሴ የእኔ
አትሂድብኝ ከእኔ
አዝማች · Chorus
አትሂድብኝ ደካማ ነኝ
ያለ አንተማ አቅም የለኝም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ባጠፋም ልጅህ ነኝ ቅጣኝ
ግን መንፈስህ እንዳይርቀኝ
የሕይወት እስትንፋሴ
ህልውናህ ነው ኢየሱሴ
ስትርቀኝ ይከፋኛል
አንተን መፍራት ይከብደኛል
የምትረዳኝ ረድኤቴ
አትሂድ ከሕይወቴ
አዝማች · Chorus
አትሂድብኝ ደካማ ነኝ
ያለ አንተማ አቅም የለኝም
ቁጥር 3 · Verse 3
ዝናህ ሀብት ሞልቶ ጐተራዬም ቢሞላም አዬ
መኖር አልችልም እኔ ስትለየኝ ከጐኔ (፪x)
መኖር ይከብደኛል ሕይወትም ይታክተኛል
መኖር አልችልም እኔ ስትለየኝ ከጎኔ (፪x)
አባብዬ የእኔ ጌታ ናፍቆቴ ነህ ጠዋትም ማታ
ህልውናህ መገኘት ደስታን አጠገበኝ ፊትህ (፪x)
ፊትህን ሳየው ውስጤን ደስታ ትሞላኛለህ
ምንም ባይኖረኝ ምንም አንተው ትበቃኛለህ (፪x)
መኖር አልችልም እኔ ስትለየኝ ከጐኔ
መኖር አልችልም እኔ ስትለየኝ ከጐኔ (፭x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ