ጊዜ አለው ለሁሉ
Gizie Alew Lehulu
ትራክ 7 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ቃልህን ሰምቼ ተጽናናሁኝና
ይፈጸማል ብዬ ነገን ጠበቅኩና
ጊዜው ሲገፋ አስጨነቀኝ
ያልከኝም ምንም አልሆነልኝ
ይልቁን መከራ ሆነብኝ
ምንድነው ጉዱ መላ በሉኝ
ወተትና ማርን የምታፈስ ሀገር
አወርሳችኋለሁ ብለህ ለእስራኤል [1]
መንገድ ሲጀምሩ መከራቸው በዛ
የተናገርካቸው ሁሉ እስኪረሳ [2]
ያልከው ግን ሌላ
የሚሆነው ሌላ (፪x)
መች በረሃ ቀሩ ቃሉ ተፈፀመ
አትዘገይም አንተ ያልከው ሁሉ ሆነ [3]
ምንም ብትዘገይም ትመጣለህና
እጠብቅሃለሁ የእኔም ቀን አለና
ያልከው ግን ሌላ
የሚሆነው ሌላ (፪x)
አንተ ያልከኝ ሌላ ነው
የሚሆንብኝ ሌላ ነው
ምንድነው ነገሩ ወዴት ነው
ሚስጥሩ አስተምረኝ
አዝማች · Chorus
(ጊዜ አለው ለሁሉም) ኧረ ነፍሴ ረጋ በዪልኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
(ጊዜ አለው ለሁሉም) ያደርገዋል እርሱ ካለኝ
(ጊዜ አለው ለሁሉም) ሳይፈፀም ጊዜው ቢገፋም
(ጊዜ አለው ለሁሉም) እጠብቃለሁ የትም አልሄድም (፪x)
ዮሴፍ ወንድሞቹ ሲሰግዱለት አየ
እንደምታከብረው እንዲነግስ አለመ [4]
ነገር ግን ሲነሳ ሊገድሉት ተነሱ
በግዞት ተጣለ ህልሞቹም ተረሱ [5]
ያልከው ግን ሌላ
የሚሆነው ሌላ (፪x)
ዘመናት ቢፈጅም ህልሙ ተፈጸመ
የማይሆን ቢመስልም እንዳየው ግን ሆነ
በለሱን የሚጠብቅ ፍሬዋን ሊበላ
ለታገሱ ሁሉ ጊዜ አለህና
ያልከው ግን ሌላ
የሚሆነው ሌላ (፪x)
አንተ ያልከኝ ሌላ ነው
የሚሆንብኝ ሌላ ነው
ምንድነው ነገሩ ወዴት ነው
ሚስጥሩ አስተምረኝ
አዝማች · Chorus
(ጊዜ አለው ለሁሉም) ኧረ ነፍሴ ረጋ በይልኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
(ጊዜ አለው ለሁሉም) ያደርገዋል እርሱ ካለኝ
(ጊዜ አለው ለሁሉም) ሳይፈፀም ጊዜው ቢገፋም
(ጊዜ አለው ለሁሉም) እጠብቃለሁ የትም አልሄድም (፪x)
አምላኬ ጊዜው ሲሄድብኝ መላ ፍለጋ
አጋር ቤት ገብቼ እንዳልጐዳ
አስተዋይ አርገኝ ትዕግስትን ስጠኝ (፪x)
ጌታዬ አንተን ተስፋ አድርጌ አላፍርምና
በራስህ ጊዜ ይሆናልና
እባክህ እርዳኝ ታጋሽ አርገኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ