ፈቶኛልና
Fetognalena
ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በባርነት በቀምበር ተይዞ
የተስፋው ሕዝብ በሃዘን ተውጦ
የሰቆቃ ጩኸቱን ሰማና
አሳረው ታደገውና
አቤት የእርሱ ሥራ
ነፃነቴን ቃሉ ነገረኝ
እኔን እመን ቀና በል አለኝ
ተፈትተሃል ምንድነው ጭንቀት
መጠራትህ ለነፃነት
አቤት የእርሱ ሥራ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከላይ ወረደ ሕዝቡን ሊያሳርፍ በመስቀል ላይ ሞቶ
(ከላይ ወረደ ሕዝቡን ሊያሳርፍ በመስቀል ላይ ሞቶ)
የታሰሩትን ነፃ ሊያወጣ መፈታትን ይዞ
(የታሰሩትን ነፃ ሊያወጣ መፈታትን ይዞ)
ቀንበር ተሰብሯል አይዞህ አትፍራ ተረጋግተህ ኑር
(ቀንበር ተሰብሯል አይዞህ አትፍራ ተረጋግተህ ኑር)
ተከፍቷል በሩ አምነህ ተራመድ አለኝ እግዚአብሔር
(ተከፍቷል በሩ አምነህ ተራመድ አለኝ እግዚአብሔር)
አዝማች · Chorus
(ፈቶኛልና) የኋላዬን አላይ
(ፈቶኛልና) የፊት የፊቴን እንጂ
(ፈቶኛልና) አዕምሮዬ ታድሷል
(ፈቶኛልና) ነፃነቴን ላውጅ
(ፈቶኛልና) በፊቱ እዘላለሁ
(ፈቶኛልና) እንደተፈታ ሰው
(ፈቶኛልና) ጠላቴም ይፈር ይፈር
(ፈቶኛልና) የፈታኝ ኢየሱስ ነው
አዝማች · Chorus
(ነፃ ላወጣን ለጌታ) ምሥጋና
(ነፃ ላወጣን ለጌታ) እልልታ
(ነፃ ላወጣን ለጌታ) ዘምሩ
(ነፃ ላወጣን ለጌታ) እልል በሉ
ቁጥር 3 · Verse 3
. (1) .
(ነፃ) ከሀጥያት (ነፃ) ከእስራት
(ነፃ) ከፍርሃት (ነፃ) ነፃ ነኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይኸው እልልታ (፰x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የፈታኝ ነገረኝ ቀሰቀሰኝና
ቀንበርህ ተሰብሯል በል ሂድ ተነሳና
ተፈቶ ዝም የለም ይሰማል ምሥጋና
የዘመናት ታሪክ ተለውጧልና
አዝማች · Chorus
ለፈታኝ (እኔ አለኝ ምሥጋና)
ላዳነኝ (እኔ አለኝ ምሥጋና)
ለጌታ (እኔ አለኝ ምሥጋና)
ለኢየሱሴ (እኔ አለኝ ምሥጋና) (፪x)
ይኸው እልልታ (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ