መድኃኒያለም
Medehanialem
ትራክ 9 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
“ስብሐተ-እግዚአብሔር ይነግር አፉየ ኩሉ ዘስጋ ይባርክ
ለሥሙ ቅዱስ ለዓለም ወለዓለመ-ዓለም”
ቁጥር 2 · Verse 2
አሜን ሀሌሉያ እያሉ
ቅዱስ አለ እርሱ ዘምሩ
ዛሬም እርሱን የምትፈሩ
አምላካችሁን አመስግኑ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከድንግል ማርያም ከብፅህት ተወልዶ
ወደ ምድር መጣ ዓለምን ሁሉ ወዶ
በመስቀሉ ስራ ሁሉን ሊያስታርቅ
የባርያን መልክ ይዞ ወረደ ያለም መድሐኒት
የድሃደግ አባት የመበለት ዳኛ
እራሱን አዋርዶ ሞተልን ስለኛ
የሞትን ጣር ሁሉ አጥፍቶ ተነሳ
የጥሉ ግድግዳ ፈረሰ ሲዖልን ድል ነሳ
ተስፋ የለኝ ብሎ ውስጡ ባዘነዉ
ሰው ለማይረዳው ልቡን ሚያልበዉ
እንባውን አብሰህ አቅፈህ ምታጽናና
ክብርና ሞገስ ይብዛልህ ምሥጋና
ቁጥር 4 · Verse 4
በአብ ቀኝ ያለው (መድኃኒያለም)
ስለ እኛ የሞተው (መድኃኒያለም)
ከሞት የተነሳው (መድኃኒያለም)
በክብር ያረገው አዬ (መድኃኒያለም)
በዙፋኑ ያለው (መድኃኒያለም)
ደግሞም የሚመጣው አዬ (መድኃኒያለም)
ቁጥር 5 · Verse 5
እግዚአብሔርን አመስግኑ
ቸርነቱን ተናገሩ (ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም)
ሰማያትን ሰራ (ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም)
ምድርን ዘረጋ (ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም)
መላዕክት ሰገዱ (ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም)
ይገባዋል አሉ (ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም)
አዝማች · Chorus
ኧኸ ኧኸ
ይገባዋል ይገባዋል
ይገባዋል ይገባዋል (ታርዷልና) (፫x)
ቁጥር 6 · Verse 6
በከበሮ (አመስግኑት)
በመሰንቆ (አመስግኑት)
በበገና (አመስግኑት)
በዕልልታ (አመስግኑት) (፪x)
አዝማች · Chorus
ኧኸ ኧኸ
ይገባዋል ይገባዋል
ይገባዋል ይገባዋል (ታርዷልና) (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ