ጌታ ከኛ ጋር
Gieta Kegna Gar
ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሊወጋኝ ጠላት ከቦኝ ፥ ሲፎክር ሲያስፈራራኝ
አምላኬን ስመለከት ፥ ልቤ ተሞላ በእምነት
የልብ ዓይኖቼን ሲያበራ ፥ አየሁ የእሳት ሰረገላ
በል ግጠማቸው ውጣና ፥ አስቀድምልኝ ምሥጋና
አዝማች · Chorus
ጌታ (ከእኛ ጋር) በመንፈሱ (ከእኛ ጋር)
ኢየሱስ (ከእኛ ጋር) በመንፈሱ (ከእኛ ጋር)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰልፉ ሲበዛ ፈራሁኝ ብዬ
አምላኬን ጠየቅኩ ምን ላድርግ ብዬ
ልጄ ምሥጋና ጀምር አለኝ
በድብቅ ጦሩ ሊፈጅልኝ
ጠላት ወደቀ (ምሥጋናን ይዤ)
ተንኮታኮተ (ምሥጋናን ይዤ)
ቃሉን ለብሼ (ምሥጋናን ይዤ)
ሰይፌን ይዤ (ምሥጋናን ይዤ)
አትደናገጥ በምትሰማው በሟርት በዛቻቸው
ከአንተ ጋር ያለው ይበልጣልና ታድያ ሳቅባቸው
ቀድሞም ጠላትህ ወድቋልና በእምነት ጀምር ምሥጋና
አዝማች · Chorus
ጌታ (ከእኛ ጋር) በመንፈሱ (ከእኛ ጋር)
ኢየሱስ (ከእኛ ጋር) በመንፈሱ (ከእኛ ጋር)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጠላቱ የተቀጣ (ጠላቱ የተቀጣ)
ለአምላኩ ክብር ያምጣ (ለአምላኩ ክብር ያምጣ)
ይደርደር በገናው (ይደርደር በገናው)
ይመታ ከበሮው (ይመታ ከበሮው )
ምሥጋና (ለእርሱ) እልልታ (ለእርሱ)
ምሥጋና (ለእርሱ) እልልታ (ለእርሱ)
ምሥጋና (ለእርሱ) እልልታ (ለእርሱ) (፪x)
(ወላይትኛ)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ