Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አለህ እግዚአብሔር

Aleh Egziabher

2019 · ትራክ 6 · 5:31 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አለህ አለህ እግዚአብሔር

አለህ አንተ እግዚአብሔር

አለህ አለህ እግዚአብሔር

ዛሬም ሰውን አልተውክም

አለህ አለህ እግዚአብሔር

አለህ አንተ እግዚአብሔር

አለህ አለህ እግዚአብሔር

ማትንቅ የሁሉ ወዳጅ

የአንተ ፍቅር በሁሉ ተፈትኖ

ወቅት ሳያሸንፈው ደካማውን ወዶ

የእናት ፍቅር እንኳን ይለወጥ ይሆናል

እንደልጅ አኳኋን ሁኔታ ይወሰናል

የማትለዋወጥ አየን አንተን ወዳጅ

እውነተኛ ወላጅ አንተ ነህ የእኛ አባት X፪

አለህ አለህ እግዚአብሔር

አለህ አንተ እግዚአብሔር

አለህ አለህ እግዚአብሔር

ዛሬም ሰውን አልተውክም

አለህ አለህ እግዚአብሔር

አለህ አንተ እግዚአብሔር

አለህ አለህ እግዚአብሔር

ማትንቅ የሁሉ ወዳጅ

ልጅን እስከመስጠት የሚወድ ፍቅር

የሕይወትን ትርጉም አቅጣጫ ሚቀይር

በዚህ ማንነትህ ረስርሳለች ነፍሴ

ትመሰክራለች ቀን ከሌት አምላኬ

የማትለዋወጥ አየን አንተን ወዳጅ

እውነተኛ ወላጅ አንተ ነህ የእኛ አባት X፪

ከተመስገን ሌላ ቃል አለ ወይ ለአንተ ሚሆንህ

ቃል አለ ወይ ለአንተ ሚሆንህ

ከተባረክ ሌላ ቃል አለ ወይ ለአንተ ምሰጥህ

ቃል አለ ወይ ለአንተ ምሰጥህ

ሕይወቴ በፍቅርህ ሞልተኸዋልና ዙፋንህን ዛሬም ይክበበው ምሥጋና

ዘመኔንን በቃልህ አስውበሃልና ዙፋንህን ዛሬም ይክበበው ምሥጋና X፪

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ