Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የነፍሴ ሐሴት)

Yenefse Hasset (feat. Kemi

2019 · ትራክ 10 · 3:45 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ነፍሴ በአንተ ሐሴት ታደርጋለች X፬

እግዚአብሔር የእኔ የእኔ ነው እያለች X፬

ዝማሬዋ ኃይሏ ጉልበት ሆነህላት

ያለፈውን ዘመን ክንድህ አሻገራት

አንተ ዘንድ እጅጉን ብዙ ኃይል አለና

እስከፍጻሜውም በቤትህ ሚያጸና

ነፍሴ በአንተ ሐሴት ታደርጋለች X፬

እግዚአብሔር የእኔ የእኔ ነው እያለች X፬

የእኔ የእኔ የእኔ የእኔ

መመኪያዬ ሁሌ ክብሬ

አንተ አይደለህ በዘመኔ

የምጠራው ዘር ማንዘሬ

ነፍሴ ምን አጣች አንተን አግኝታ

ሆንክላት በጐ ሆንክላት ጋሻ

ስለዚህ በእዚህ ለእግዚአብሔር እንደዚህ

ያምርብሻል ውዳሴ ምሥጋና ነፍሴ ስታፈልቂ

ምንም የሌላትን ምንኛ ረዳሃት

ከአንተ የተነሳ እዚህ አደረስካት

በአመራርህ ጌታ እጅግ እረክታለች

አምላኬ መሪዬ እርሱ ነው ትላለች

ነፍሴ በአንተ ሐሴት ታደርጋለች X፬

እግዚአብሔር የእኔ የእኔ ነው እያለች X፬

እግዚአብሔር ክብሬ ክብሬ ነው እያለች X፬

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ