እግዚአብሔር የለም?
Egziabher Yelem?
2019 · 4:06 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚአብሔር የለም እንዴት ትለኛለህ
መኖሩን ዘወትር በዙሪያህ እያየህ
ነፍስህን ሸጠሃት ለዓለም ፍልስፍና
በከንቱ ሳትለፋ ወንድሜ ቶሎ ና
የፍጥረት ፈጣሪ ከመሠረቱ
ቃሉ ሕያው ነው ሁሌም ክንደ ብርቱ
የመጀመሪያ የመጨረሻም ነው
አልፋና ኦሜጋ ሚመስለው የሌለው
አዝማች · Chorus
አለ አለ
እግዚአብሔር አለ
ቁጥር 2 · Verse 2
የዚህች ዓለም ሕይወት ሆኖብን ብርቱ ሰልፍ
ከብዶ ያስጨነቀን መስሎን ማይታለፍ
የተደራረበው የመከራ ጐርፍም
ተስፋ አስቆርጦ የለም ሊያስብለን
በሁኔታ አይገመት በመንገዱ እጅግ ጻድቅ
ቃል የገባውን አለሁ ብሎ
ዛሬም አለ ሚደርስ ቶሎ
አዝማች · Chorus
አለ አለ
እግዚአብሔር አለ
ቁጥር 3 · Verse 3
ከጥንት የነበረ ያለ የሚኖረው
ሁኔታ ማይለውጠው እርሱ እግዚአብሔር ነው
ከጥንት የነበረ ያለ የሚኖረው
ልብን ሚፈውሰው እርሱ እግዚአብሔር ነው
በዘመን ፍጻሜ በዓለም መጨረሻ
ሁሉም ተደምድሞ ላይኖር መመለሻ
በፊቱ ስንቆም ሰርቶ ባኖረን ፊት
ትርፉ ጸጸት እንዳይሆን አርፍደን ለጥቂት
ዛሬ ቀን ሳለ ፈጣሪን እናስብ
የፍቅር ጥሪውን ልባችን ይቀበልው
ለዚህች አጭር ሕይወት ምትጠፋ እንደ ጤዛ
ቀን ሳለ እንመለስ አንሞኝ አንልፋ
ቁጥር 4 · Verse 4
አለ እግዚአብሔር አለ
አዎ
አለ እግዚአብሔር አለ
ታሪክ ይናገራል መጸሃፉ
የለም ያሉት ሁሉ እንደጠፉ ፪X
አለ እግዚአብሔር አለ
አዎ
አለ እግዚአብሔር አለ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ