Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ይበሉ

Yibelu

2019 · ትራክ 9 · 3:55 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እስኪ ይናገሩ የተሻገርኳቸው እነዚያ መንገዶች

ፍቅርና ምሕረትህ የደጋገፈኝ እነዚያ ቀናቶች

እስኪ ይናገሩ የተሻገርኳቸው እነዚያ መንገዶች

በእሳት አምድ ደመና ክንድህ ያሳለፈኝ እነዚያ ቀናቶች

ይበሉ

እንደ እግዚአብሔር ያለ የለም

ይበሉ

እንደ ጌታ ያለ የለም X፪

ነፍሴ በእግዚአብሔር አምናለችና አታፍርም

አምናለችና አታፍርም

ትልቅነቱን ታውቃለችና አታፍርም

ታውቃለችና አታፍርም

ይረዳታል ያግዛታል ከለላዋም ሆኖላታል

ይረዳታል ያግዛታል ማዳኑንም ያሳያታል

እላለሁ

እንደ እግዚአብሔር ያለ የለም

እላለሁ

እንደ ጌታ ያለ የለም X፪

ሁኔታ እየመጣ ሲያነጋግረኝ

ሲያነጋግረኝ

የዛሬውስ መውጫሽ ምን ይሆን ቢለኝ

ምን ይሆን ቢለኝ X፪

አሄ እግዚአብሔርን ይዤ እኔ ምን ሆናለሁ

አሄ እረድኤቴ ጋሻ ሆኖልኝ እያየሁ

አሄ እግዚአብሔርን ይዤ እኔ ምን ሆናለሁ

አሄ የከፍታዬ ሰይፍ ሆኖልኝ እያየሁ

አሄ እግዚአብሔርን ይዤ እኔ ምን ሆናለሁ

አሄ ነገሬን በእጆቹ ይዞልኝ እያየሁ

እላለሁ

እንደ እግዚአብሔር ያለ የለም

እላለሁ

እንደ ጌታ ያለ የለም X፪

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ