አመልካለሁ ይህን ጌታ
Amelkalehu Yehen Gieta
2012 · ትራክ 11 · 5:01 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አመልከዋለሁ ይህንን ጌታ
ሰግድለታለሁኝ በደስታ
ክብርን እሰጣለሁ ሁሌ እኔ ዝቅ ብዬ
ጌታዬን ልሾመው በሁለንተናዬ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ተስፋ ያደረኩት መቼ ይተዋኛል
በብዙ ሰላሙ እርሱ ይመራኛል
የልዑል መጠጊያ ሁሉም በሚችለው
በዘለዓለም ኃይሉ በእርሱ እታመናለሁ
አዝማች · Chorus
አመልከዋለሁ ይህንን ጌታ
ሰግድለታለሁኝ በደስታ
ክብርን እሰጣለሁ ሁሌ እኔ ዝቅ ብዬ
ጌታዬን ልሾመው በሁለንተናዬ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በለቅሶ ሸለቆ ብሆን በመከራ
በረከት ይሆናል በወሰንው ስፍራ
ሁሌ የምኮራበት ለእኔ ዋስትናዬ
የማምለጫ ዓለቴ መከታ ጋሻዬ
አዝማች · Chorus
አመልከዋለሁ ይህንን ጌታ
ሰግድለታለሁኝ በደስታ
ክብርን እሰጣለሁ ሁሌ እኔ ዝቅ ብዬ
ጌታዬን ልሾመው በሁለንተናዬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አልደራደርም ከጠላቴ ጋራ
የቆመውም ችግር ቢሆንም በተራ
ልዩነት ይሆናል በአረማመዴ
ከቶም አይነካኝም አለና ጌታዬ
አዝማች · Chorus
አመልከዋለሁ ይህንን ጌታ
ሰግድለታለሁኝ በደስታ
ክብርን እሰጣለሁ ሁሌ እኔ ዝቅ ብዬ
ጌታዬን ልሾመው በሁለንተናዬ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እርሱን ተማምኜ ተደግፌዋለሁ
እግዚአብሔር መልካም ነው በጥላው አድራለሁ
ዛሬ የሚታየውን ምድራዊው ችግሬ
እንዲህ አይቀጥልም በላይ ነው አገሬ
አዝማች · Chorus
አመልከዋለሁ ይህንን ጌታ
ሰግድለታለሁኝ በደስታ
ክብርን እሰጣለሁ ሁሌ እኔ ዝቅ ብዬ
ጌታዬን ልሾመው በሁለንተናዬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ