በዓለም ተጥዬ
Bealem Teteyie
2012 · ትራክ 7 · 6:32 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በዓለም ተጥዬ ዋጋም ሳይኖረኝ
በሰውም ተንቄ ስፍራንም ሳላገኝ
ቃሉን ሲያወጣ ከማደሪያው ቦታ
ታላቅም ሠራዊት አድርጐኛል ጌታ (፪x)
ሕይወቴን ሊጐዳ ዝቶብኝ ጠላቴ
እግዚአብሔር አዳነኝ ጥሶ ገብቶ ቤቴ
እኔም አመልካለሁ ይህን ታላቅ ጌታ
አውጥቶኛልና ከጭንቅ ከመከራ
አዝማች · Chorus
የውለታው ብዛት ሳስብ ይገርመኛል
ጌታ ለእኔ ያደረገው እጅግ ይደንቀኛል (፪x)
ምኔን አይተህ ልበል
ምኔ ስቦት ይሆን እንዲህ የወደደኝ
እንዲሁ በፍቅሩ የእራሱ አደረገኝ
ከጠላት መንጋጋ ፈልቅቆ አስመለጠኝ
ከዓለም ለይቶ ለእራሱ አደረገኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
አይተወኝም እርሱ መቼም አይረሳኝም
በፍቅሩ እኔን ገዝቶ ልቤን ማርኮ
አምነዋለሁ እርሱን ዘለዓለማዊ ነው
አይጥለኝም ሁሌ ታማኝ ወዳጄ ነው
አዝማች · Chorus
የውለታው ብዛት ሳስብ ይገርመኛል
ጌታ ለእኔ ያደረገው እጅግ ይደንቀኛል (፪x)
ምኔን አይተህ ልበል
ምኔ ስቦት ይሆን እንዲህ የወደደኝ
እንዲሁ በፍቅሩ የእራሱ አደረገኝ
ከጠላት መንጋጋ ፈልቅቆ አስመለጠኝ
ከዓለም ለይቶ ለእራሱ አደረገኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
ደግፎ ያቆመኝ እኔን በምህረት
የማውቀው ጌታን ነው ደግሞም በቸርነት
መጣ እኔንም አይቶ ያነሳኝ እርሱ ነው
ዛሬም ቢሆን ነገ በእርሱ እታመናለሁ
አዝማች · Chorus
የውለታው ብዛት ሳስብ ይገርመኛል
ጌታ ለእኔ ያደረገው እጅግ ይደንቀኛል (፪x)
ምኔን አይተህ ልበል
ምኔ ስቦት ይሆን እንዲህ የወደደኝ
እንዲሁ በፍቅሩ የእራሱ አደረገኝ
ከጠላት መንጋጋ ፈልቅቆ አስመለጠኝ
ከዓለም ለይቶ ለእራሱ አደረገኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ