አለኝ የምለው
Alegn Yemelew
2012 · ትራክ 3 · 6:15 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አለኝ የምለው በዚህ በምድር ላይ
አንድም የለኝም ጌታ ከአንተ በላይ
አልችልምና ያለአንተ መኖር
መንፈስህ ሁሉ በሕይወቴ ይኑር (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ቁስለኛውን ልቤን የሚጠግነው
የነፍሴን ህመም የሚፈውሰው
መንፈስህ ነው ተስፋ ያደረኩት
በምድር ያለውን አይደለም ያየሁት
የተሰበረውን አንተ የምትሻውን
መስዕዋት አድርገህ የምታሸተውን
ይህን መንፈስ ስጠኝ እለም
ጸሎቴ ይህ ነው እለምንሃለሁ
አንተን የሚፈልግ ልብን ፍጠርልኝ
የቀናውን መንፈስ በውስጤ አድስልኝ
ባክህን ጌታ ከፊትህ አትጣለኝ
ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ አትውሰድብኝ (፫x)
አዝማች · Chorus
አለኝ የምለው በዚህ በምድር ላይ
አንድም የለኝም ጌታ ከአንተ በላይ
አልችልምና ያለአንተ መኖር
መንፈስህ ሁሉ በሕይወቴ ይኑር (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
መንገዴ ይሄ ነው ብሎ ያሳየኝ
የሕይወቴ መሪ ለእኔ የሆነልኝ
መንፈስህ ብቻ እረፍትን የሰጠኝ
ከመከራ ስጋት እኔን ያሳረፈኝ
ልክ እንደነኤልሳ እንደ ኤልያስ
ልቤ ታዛዥ ይሁን ለአንተ መንፈስ
እንደ ወደድክ አርፈህ በእኔ እንድትሰራ
ሕይወቴን ሰጠሁህ ጌታ ሆይ አደራ
ብርና ወርቅ ለእኔ ሰላም አልሆነኝም
ሃብትና ንብረትም እረፍት አልሰጠኝም
ውስጣዊው እርካታ የልቤ ደስታ
አንተ ነህ የሰጠኸኝ ክበር የእኔ ጌታ
ክበር ክብር የእኔ ጌታ (፪x)
አዝማች · Chorus
አለኝ የምለው በዚህ በምድር ላይ
አንድም የለኝም ጌታ ከአንተ በላይ
አልችልምና ያለአንተ መኖር
መንፈስህ ሁሉ በሕይወቴ ይኑር (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ