ኧረ አመስግኑልኝ
Ere Amesgenulegn
2012 · ትራክ 1 · 5:11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ማህጸኗ ቢደርቅ . (1) . ይዟት
ተስፋዋ ተሟጦ ልጅ መውለድ ቢያቅታት
የአብርሃም አምላክ መቼ አረጀና
ይወለዳል ይስሃቅ እርሱ ብሏልና (፪x)
አዝማች · Chorus
ኧረ አመስግኑልኝ ይህን ጀግና ጌታ
ከፍ ይበል ይባረክ ይንገሥ በዕልልታ
እርሱ ብቻ እኮ ነው የእኛስ አምላካችን
ሲሰራ ስላየን ዛሬም በሕይወታችን
እርሱ ብቻ እኮ ነው የእኛስ አምላካችን
ሲሰራ ስላየን ዛሬም በሕይወታችን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አብርሃም ቢያረጀም ሳራም ብትደካክም
ሁኔታውን አይተው የማይሆን ቢመስልም
ለጌታ ምን አቅቶት ምን ተስኖት ያውቃል
ይስሃቅን ሰጥቷቸው አስደንቋቸዋል (፪x)
አዝማች · Chorus
ኧረ አመስግኑልኝ ይህን ጀግና ጌታ
ከፍ ይበል ይባረክ ይንገሥ በዕልልታ
እርሱ ብቻ እኮ ነው የእኛስ አምላካችን
ሲሰራ ስላየን ዛሬም በሕይወታችን
እርሱ ብቻ እኮ ነው የእኛስ አምላካችን
ሲሰራ ስላየን ዛሬም በሕይወታችን (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የሚያስፈልግህን በጊዜው ያደርጋል
ታምነህ ከተቀመጥክ ቃሉንም ያከብራል
አድራሻህን አድርገው ከዙፋኑ ሥር
ፈጥኖ ይረዳሃል ታማኝ ነው እግዚአብሔር
አድራሻሽን አድርጊው ከዙፋኑ ሥር
ፈጥኖ ይረዳሻል ታማኝ ነው እግዚአብሔር
አዝማች · Chorus
ኧረ አመስግኑልኝ ይህን ጀግና ጌታ
ከፍ ይበል ይባረክ ይንገሥ በዕልልታ
እርሱ ብቻ እኮ ነው የእኛስ አምላካችን
ሲሰራ ስላየን ዛሬም በሕይወታችን
እርሱ ብቻ እኮ ነው የእኛስ አምላካችን
ሲሰራ ስላየን ዛሬም በሕይወታችን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ