ሰዎች እንዲፈርድብኝ
Sewoch Endiferdebegn
2012 · ትራክ 12 · 5:47 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሰዎች እንዲፈርድብኝ ጣሉኝ ከእግሩ ሥር
ትሙትልን አሉ በድንጋይ ትወገር
ያልጠበኩትን ቃል ጌታ ተናገረ
ኃጥያትን አትስሪ ምሬሻለሁ አለ
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔማ አልታይም በባዶ እጆቼ
ይዤ መጥቻለሁ መላ እኔነቴን
ሁለንተናዬን ለእርሱ ሰጥቻለሁ
መሷቴን ይዤ በፊቱ እቀርባለሁ
አዝማች · Chorus
ሰዎች እንዲፈርድብኝ ጣሉኝ ከእግሩ ሥር
ትሙትልን አሉ በድንጋይ ትወገር
ያልጠበኩትን ቃል ጌታ ተናገረ
ኃጥያትን አትስሪ ምሬሻለሁ አለ
ቁጥር 2 · Verse 2
አትዎጭም እያሉ ሲዘባበቱብኝ
አምላኬ ዙፋን ስር እራሴን አዋረድኩኝ
በሮችን ከፋፍቶ መዝሙርን ሰጥቶኛል
ጠላትም እያየ እኔን አክብሮኛል
አዝማች · Chorus
ሰዎች እንዲፈርድብኝ ጣሉኝ ከእግሩ ሥር
ትሙትልን አሉ በድንጋይ ትወገር
ያልጠበኩትን ቃል ጌታ ተናገረ
ኃጥያትን አትስሪ ምሬሻለሁ አለ
ቁጥር 3 · Verse 3
አድርገህልኛል ከአዕምሮዬ በላይ
ሥምህን ላሞጋግሰው በምድር በሠማይ
ከሕይወት እንጀራ እኔን አጥግበኸኛል
በመስቀል በመሞት ሕይወት ሆነኸኛል
አዝማች · Chorus
ሰዎች እንዲፈርድብኝ ጣሉኝ ከእግሩ ሥር
ትሙትልን አሉ በድንጋይ ትወገር
ያልጠበኩትን ቃል ጌታ ተናገረ
ኃጥያትን አትስሪ ምሬሻለሁ አለ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ