በሥሙ ታምኜ
Besemu Tamegnie
2012 · ትራክ 9 · 5:41 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም
በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም
ሥሙንም ጠርቼ እኔ አላጣሁም
ከመልካም ነገር ፈጽሞ አልጐደልኩም (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ውድቀቴን ሲጠብቅ አሁንም ያ ክፉ
አታልፊውም ሲለኝ ቀኖቹም ሲከፉ
የነፍሴ እረኛ ኢየሱስ ደረሰና
እኔን አሻገረኝ ታሪክ ለወጠና
አዝማች · Chorus
በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም
በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም
ሥሙንም ጠርቼ እኔ አላጣሁም
ከመልካም ነገር ፈጽሞ አልጐደልኩም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጠላት ሲያስለቅሰኝ ሸለቆ እያሳየ
እግዚአብሔር ከሠማይ ሰምቶ ዘንበል አለ
እንባዬን አብሶ ደስታን አለበሰኝ
ለልቤ መጽናናት በእርሱ ላይ ሆነልኝ
አዝማች · Chorus
በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም
በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም
ሥሙንም ጠርቼ እኔ አላጣሁም
ከመልካም ነገር ፈጽሞ አልጐደልኩም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ገበናዬን ሸፊኝ ሚስጥር ተካፋዬ
ጉድለቴን ሞላልኝ በእርሱ በጌታዬ
በሠማዩ ስፍራ በመንፈስ ባርኮኛል
የመንግሥቱ ወራሽ ርስቱ አድርጐኛል
አዝማች · Chorus
በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም
በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም
ሥሙንም ጠርቼ እኔ አላጣሁም
ከመልካም ነገር ፈጽሞ አልጐደልኩም (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ሰምቶ የሚመልስ አይቶ የሚራራ
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለምና
ታዲያ ለዚህ ጌታ ላብዛለት ምሥጋና
ክብር ያገኘሁት በአምላኬ ነውና
አዝማች · Chorus
በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም
በእግዚአብሔር በሥሙ ታምኜ አላፈርኩም
ሥሙንም ጠርቼ እኔ አላጣሁም
ከመልካም ነገር ፈጽሞ አልጐደልኩም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ