አካሄዴን ጌታ
Akahiedien Gieta
2012 · ትራክ 8 · 4:44 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አካሄዴን ጌታ እንደቃልህ አቅና
ፀጋህ ይደግፈኝ ደካማ ነኝና
ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው
እንክርዳድን ከስንዴ የሚለይ ነው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ከማር ከወለላ ሁሉ የሚጣፍጠው
ከነገሮች ሁሉ እጅጉን የሚበልጥ
አለኝ የሕይወት ቃል የተከበረው
ጌታም አጽንቶታትል የማይሻር ነው
አዝማች · Chorus
አካሄዴን ጌታ እንደቃልህ አቅና
ፀጋህ ይደግፈኝ ደካማ ነኝና
ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው
እንክርዳድን ከስንዴ የሚለይ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በሕይወቴ ዘመን አንተን እንዳመልክህ
ጌታ በኑሮዬ ቃልህን አብራልኝ
ከአመጸኛ ከንፈር ከሸንጋይ አንደበት
ጌታ ሆይ ጠብቀኝ እንደ ቃልህ እንድኖር
አዝማች · Chorus
አካሄዴን ጌታ እንደቃልህ አቅና
ፀጋህ ይደግፈኝ ደካማ ነኝና
ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው
እንክርዳድን ከስንዴ የሚለይ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ባክህ ተናገረኝ ዝምም አትበለኝ
ቃልህን አብራልኝ ከፊትህ አትጣለኝ
ጌታ ሆይ ቃልህ ተስፋ አደርገዋለሁ
በናፍቆት በጉጉት እጠባበቃለሁ
አዝማች · Chorus
አካሄዴን ጌታ እንደቃልህ አቅና
ፀጋህ ይደግፈኝ ደካማ ነኝና
ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው
እንክርዳድን ከስንዴ የሚለይ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ