አመልክሃለሁ የእኔ ጌታ
Amelkehalehu Yenie Gieta
2005 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በሰማይ አየሁ አንተን የሚመስልህ የለም
በምድርም አየሁ አንተን የሚመስልህ የለም
ከምድር በታችም አየሁ አንተን የሚመስልህ የለም
በልጠህብኛልና መርጬሃለሁ
ተሽለኸኛልና ተከትዬሃለሁ
በዘመኔ ሁሉ ለአንተ እገዛለሁ
ለአንተ እገዛለሁ (፬x)
አዝማች · Chorus
አመልክሃለሁ የእኔ ጌታ
ቁጥር 2 · Verse 2
አመልክሃለሁ የእኔ ወዳጅ
እንደአንተ ያለ ማንም የለም
ለእኔ የሚበጅ (፪x)
አንተን ብቻ ጌታ አመልካለሁ
ለአንተ ብቻ ኢየሱስ እገዛለሁ
ከአንተ ውጬ ሌላ ሌላ አምላክ የለኝም (፬x)
ከማን ጋር አንተን ጌታ አስተካክላለሁ
ከምን ጋር አንተን ኢየሱስ አመሳስላለሁ
ከየትኛውስ ጋራ አንተን አወዳድራለሁ
ከብርና ከወርቅ ፍቅርህ በልጦብኛል
ከሃጣን ድንኳን ይልቅ ቤትህ ተሽሎኛል
ወደአንተ መጠጋቴ ለእኔስ በጅቶኛል (፬x)
አዝማች · Chorus
አመልክሃለሁ (የእኔ ጌታ) የእኔ ጌታ
ቁጥር 3 · Verse 3
አመልክሃለሁ (የእኔ ወዳጅ) የእኔ ወዳጅ (የእኔ ወዳጅ)
እንደአንተ ያለ ማንም የለም
ለእኔ የሚበጅ (፬x)
አንተን ብቻ ጌታ አመልካለሁ
ለአንተ ብቻ ኢየሱስ እገዛለሁ
ከአንተ ውጬ ሌላ ሌላ አምላክ የለኝም (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ