Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መንግሥት የአንተ ነው

Mengest Yeante New

2005 · ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

መንግሥት የአንተ ነው ስልጣንም የአንተ ነው

ሃይልም የአንተ ነው ብርታትም የአንተ ነው (፪x)

ምሥጋናን ለስምህ እናቀርባለን

አምልኮን በፊትህ እንሰዋለን

ይገባሃልና እናከብርሃለን ኦ እናከብርሃለን (፬x)

ምሥጋናን ለስምህ እናቀርባለን

አምልኮን በፊትህ እንሰዋለን

ይገባሃልና እናከብርሃለን ኦ እናከብርሃለን (፬x)

ባለ ብዙ ግርማ ባለ ብዙ ሞገስ

በሁሉ ላይ ከፍ ያልክ

ከፍ ያልክ የነገስክ

አንተ ነህ እግዚአብሔር የዘለዓለም ንጉሥ (፪x)

መንግሥት የአንተ ነው ስልጣንም የአንተ ነው

ሃይልም የአንተ ነው ብርታትም የአንተ ነው (፪x)

ምሥጋናን ለስምህ እናቀርባለን

አምልኮን በፊትህ እንሰዋለን

ይገባሃልና እናከብርሃለን ኦ እናከብርሃለን (፬x)

የስልጣንን በትር በእጅህ ይዘሃል

ሁሉን ከእግርህ በታች በሃይልህ ገዝተሃል

ማን ይቋቋመሃል ማንስ ይረታሃል (፪x)

ምሥጋናችንን እናበዛለን በክብር ላይ ክብር እንጨምራለን

ይሄ ሁሉ ያንስብሃል ከዚህ በላይ ክብር ይገባሃል (፪x)

ይገባሃል (፬x) ይገባሃል (፬x)

ምሥጋናችንን እናበዛለን በክብር ላይ ክብር እንጨምራለን

ኢሄ ሁሉ ያንስብሃል ከዚህ በላይ ክብር ይገባሃል (፪x)

ይገባሃል (፬x) ይገባሃል (፬x)

ይገባሃል (፬x) ይገባሃል (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ