በእግዚአብሔር የተወደደ
Begziabhier Yetewedede
2005 · ትራክ 6 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በእግዚአብሔር የተወደደ በእርሱ ዘንድ ይኖራል (፪x)
ከትከሻው መሃል ተማምኖ ያድራል (፪x)
ለሚታመኑበት መታመኛ (ኦሆ መታመኛ)
ነውና የሚያኮራ መልካም እረኛ (ኦሆ መልካም እረኛ)
እኔም ከጥላው በታች ተጠልያለሁ (ኦሆ ተጠልያለሁ)
ፅኑ ክንዱን ተደግፌ አመልከዋለሁ (ኦሆ አመልከዋለሁ)
ቁጥር 1 · Verse 1
አምላኬ መታመኛዬ በእርሱ እደገፋለሁ
የፀና ግንብ ነውና በሥሙ እጓደዳለሁ
ገና ነፍሴ ትጠግባለች ከማያልቀው ቸርነቱ
በዘይት ሊያለመልመኝ ተክሎኛል እና በቤቱ
እርሱን ተማምኜው እኖራለሁ
በክንፉቹ ጥላ ስር አርፌያለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
በእግዚአብሔር የተወደደ በእርሱ ዘንድ ይኖራል (፪x)
ከትከሻው መሃል ተማምኖ ያድራል (፪x)
ለሚታመኑበት መታመኛ (ኦሆ መታመኛ)
ነውና የሚያኮራ መልካም እረኛ (ኦሆ መልካም እረኛ)
እኔም ከጥላው በታች ተጠልያለሁ (ኦሆ ተጠልያለሁ)
ፅኑ ክንዱን ተደግፌ አመልከዋለሁ (ኦሆ አመልከዋለሁ)
ቁጥር 2 · Verse 2
የሕይወትን ምንጭ አግኝቼ ከተድላው ፈሳሽ ጠጥቼ
ዳግመኛ እኔ አልጠማም ረቻለሁ ለዘለዓለም
በብርሃኑ ብርሃን አየሁ ጨለማውም ተሸነፈ
ተማምኜ እኖራለሁ ልቤ በእርሱ ስላረፈ
እርሱን ተማምኜው እኖራለሁ
በክንፉቹ ጥላ ስር አርፌያለሁ (፬x)
ለሚታመኑበት መታመኛ (ኦሆ መታመኛ)
ነውና የሚያኮራ መልካም እረኛ (ኦሆ መልካም እረኛ)
እኔም ከጥላው በታች ተጠልያለሁ (ኦሆ ተጠልያለሁ)
ፅኑ ክንዱን ተደግፌ አመልከዋለሁ (ኦሆ አመልከዋለሁ)
እርሱን ተማምኜው እኖራለሁ
በክንፉቹ ጥላ ስር አርፌያለሁ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ