ከሁሉ በላይ ነህ ጌታ
Kehulu Belay Neh Gieta
2005 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰላምህ በዝቶልኛል አንተን ከአገኘሁ ጀምሮ
ሕይወቴ ተለውጧል ተቀይሯል የእኔስ ኑሮ
አንተን በመከተሌ ከአንተም ጋር በመሆኔ
ተጸጽቼ አላውቅም ጌታ አንተን በማመኔ (፭x)
አዝማች · Chorus
የሕይወትን መንገድ አሳየኽኝ
ከፊትህ ጋር ደስታ አጠገብከኝ
መልካምነትህን አበዛህ በዘመኔ
ከሁሉም በላይ ሆንክልኝ መድህኔ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከሁሉ በላይ ነህ ጌታ ከሁሉ በላይ
ከሁሉ በላይ ነህ ኢየሱስ ከሁሉ በላይ (፪x)
የጐደለብኝ የለም ሁሉ ሞላልኝ እንጂ
በረከት እንደሁ አያልቅም ከአንተ ቤት ከአንተ ደጅ
የሰላም አለቃ ሆይ የሰላሜ ምንጭ ነህ
ማንም አይመጥንህም ከምርጦች ሁሉ ልዩ ነህ (፭x)
አዝማች · Chorus
የሕይወትን መንገድ አሳየኽኝ
ከፊትህ ጋር ደስታ አጠገብከኝ
መልካምነትህን አበዛህ በዘመኔ
ከሁሉም በላይ ሆንክልኝ መድህኔ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከሁሉ በላይ (በላይ በላይ) ነህ ጌታ ከሁሉ በላይ
ከሁሉ በላይ (ከሁሉ በላይ) ነህ ኢየሱስ ከሁሉ በላይ (ጌታ) (፪x)
ከምን ጋር ላወዳድርህ ከማን ጋር ላስተካክልህ
ከሚታይ ከማይታየው ከሁሉ ትበልጣለህ
ከሁሉ ትበልጣለህ (አው ከሁሉ) ከሁሉ ትሻላለህ (ሁሁ)
እድል ፈንታዬ ጌታ (እድል ፈንታዬ ጌታ) ለዘለዓለም ምርጫዬ ነህ (፭x)
አዝማች · Chorus
የሕይወትን መንገድ አሳየኽኝ
ከፊትህ ጋር ደስታ አጠገብከኝ
መልካምነትህን አበዛህ በዘመኔ
ከሁሉም በላይ ሆንክልኝ መድህኔ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከሁሉ በላይ (ኦ አንተ ከሁሉ በላይ) ነህ ጌታ
ከሁሉ በላይ (ኢየሱስ ከሁሉ በላይ)
ከሁሉ በላይ (ቃልህ ከሁሉ በላይ) ነህ ኢየሱስ ከሁሉ በላይ
(ክብርህ ከሁሉ በላይ መንግሥትህ ከሁሉ በላይ)
ከሁሉ በላይ (ሥጋህ ከሁሉ በላይ) ነህ ጌታ
ከሁሉ በላይ (ፍቅርህ ከሁሉ በላይ)
ከሁሉ በላይ (ኦ አንተ ከሁሉ በላይ) ነህ ኢየሱስ
ከሁሉ በላይ (በላይ በላይ) (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ