ነፍሴ ጠዋት ማታ
Nefsie Tewat Mata
2005 · ትራክ 11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ታስተማምናለህ ጌታዬ እኔም ታመንኩብህ
ታስተማምናለህ ብቻህን እኔን ተደገፍኩብህ (፪x)
ታምኜብሃለሁ ተደግፌሃለሁ
ዘመኔን በሙሉ በአንተ እመካለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ነፍሴ ጠዋት ማታ አንተን ታከብራለች
በቀን በሌሊትም ትባርክሃለች (፪x)
የመኖሬ ትርጉም የሕይወቴ መሰረት
አንተ ብቻ ነህ ጌታዬ የጸናሁብህ አለት (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ለምን እንደምኖር አውቃለሁ አንተን ስላገኘሁ
ለሕይወቴ ትርጉምን ሰጥተሃል ልቤን አሳርፈሃል
አርፌብሃለሁ ረክቼብሃለሁ
ከቤትህ ጠል ጠጥቼ እኔስ እፎይ ብያለሁ (፪x)
እግሮቼ በዓለት ላይ ቆመዋል
እኔ አልናወጥም
አረማመዴም ጸንቶልናል መሰረቴ አይወድቅም
የማዕዘን ድንጋይ የሕይወቴ እራስ
ብቃቴም ጉልበቴም አንተ ነህ ኢየሱስ (፪x)
አዝማች · Chorus
ነፍሴ ጠዋት ማታ አንተን ታከብራለች
በቀን በሌሊትም ትባርክሃለች (፪x)
የመኖሬ ትርጉም የሕይወቴ መሰረት
አንተ ብቻ ነህ ጌታዬ የጸናሁብህ አለት (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ