አምላኬ መታመኛዬ ነው
Amlakie Metamegnayie New
2005 · ትራክ 2 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አምላኬ መታመኛዬ ነው
አምላኬ መሸሸጊያዬ ነው (፪x)
በልዑል መጠጊያ እኖራለው
ሁሉን በሚችል ጥላ ስር አድራለሁ
እግዚአብሔር ለእኔ መታመኛዬ ነው
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚአብሔር ለእኔ መሸሸጊያዬ ነው ፣ መሸሸጊያዬ ነው (፪x)
ከክንፎቹ በታች እተማመናለሁ
የሌሊቱን ግርማ መቼ እፈራለሁ (፪x)
እውነት እንደጋሻ ዙሪያዬን ከቦኛል
በመንገዴ ሁሉ ጌታ ይመራኛል
አዝማች · Chorus
አምላኬ መታመኛዬ ነው
አምላኬ መሸሸጊያዬ ነው (፪x)
በልዑል መጠጊያ እኖራለው
ሁሉን በሚችል ጥላ ስር አድራለሁ
እግዚአብሔር ለእኔ መታመኛዬ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
እግዚአብሔር ለእኔ መሸሸጊያዬ ነው ፣ መሸሸጊያዬ ነው (፪x)
በመከራዬ ቀን ከእኔ ጋራ ሆኖ
ማዳኑን አሳየኝ ምህረቱን አግንኖ (፪x)
በጠራሁት ጊዜ ፈጥኖ መለሰልኝ
እንዳልሰናከል በእጆቹ አነሳኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
አምላኬ መታመኛዬ ነው
አምላኬ መሸሸጊያዬ ነው (፪x)
በልዑል መጠጊያ እኖራለው
ሁሉን በሚችል ጥላ ስር አድራለሁ
እግዚአብሔር ለእኔ መታመኛዬ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እግዚአብሔር ለእኔ መሸሸጊያዬ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ለእኔ መታመኛዬ ነው (፪x)
እግዚአብሔር ለእኔ መሸሸጊያዬ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ