ስሙን አከብራለሁ
Semun Akebralehu
2005 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በሃዘን ፈንታ ደስታ
በለቅሶም ምትክ ዕልልታ
ሁሉንም መልካም አደረገው
ክፉውን ለበጐ ቀየረው (፪x)
አዝማች · Chorus
ምን ልበል ሌላማ ሌላማ
ምሥጋናዬን/አምልኮዬን ለጌታ ላሰማ (፪x)
በምሥጋና ስሙን አከብራለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እጅግ እጅግ ብዙ ነው
ለእኔ ያደረገው ፣ ለእኔ ያደረገው
እጅግ እጅግ ብዙ ነው
ለእኔ ያደረገው ፣ ለእኔ ያደረገው
የተዘጋውን ደጅ ከፈተው
የነሃሱንም መዝጊያ ሰበረው
መወርወሪያዎቹን ቆራርጦ
አሳለፈኝ ከፊቴ ወጥቶ
አዝማች · Chorus
ምን ልበል ሌላማ ሌላማ
ምሥጋናዬን/አምልኮዬን ለጌታ ላሰማ (፪x)
በምሥጋና ስሙን አከብራለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እጅግ እጅግ ብዙ ነው
ለእኔ ያደረገው ፣ ለእኔ ያደረገው
እጅግ እጅግ ብዙ ነው
ለእኔ ያደረገው ፣ ለእኔ ያደረገው
በከበረው ደሙ ቀድሶ
መንፈሱን በላዬ አፍሶ
ሕይወቴን በፍቅሩ ቀየረው
ታሪኬን እንዲህ አሳመረው (፪x)
አዝማች · Chorus
ምን ልበል ሌላማ ሌላማ
ምሥጋናዬን/አምልኮዬን ለጌታ ላሰማ (፪x)
በምሥጋና ስሙን አከብራለሁ
ቁጥር 4 · Verse 4
በምሥጋና ስሙን አከብራለሁ
እጅግ እጅግ ብዙ ነው
ለእኔ ያደረገው ፣ ለእኔ ያደረገው (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ