Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አምላኬን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ

Amlakien Hulgizie Ebarekewalehu

2001 · ትራክ 2 · 6:01 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አምላኬን ሁልጊዜ አባርከዋለሁ

ምሥጋናው ዘወተር ዘወትር በአፌ ነው (፪x)

በጠዋት በማታ በቀን በሌሊት

ምሥጋናዬ ይድረስ ዘወትር በእርሱ ፊት

የአንደበቴን ፍሬ ከቶ አልቆጥብም

ብዙ አድርጐልኛል አሃሃ ችዬ ዝም አልልም

አምላኬን ሁልጊዜ አባርከዋለሁ

ምሥጋናው ዘወትር ዘወትር በአፌ ነው (፪x)

የሕይወቴ ጋሻ ተገን ሆኖልኛል

ስወጣም ሰገባም እረፍቱ ከቦኛል

እርሱን ለማመስገን በገናዬን ላንሳ

ያደረገልኝን በፍፁም ሳልረሳ

አምላኬን ሁልጊዜ አባርከዋለሁ

ምሥጋናው ዘወትር ዘወትር በአፌ ነው (፪x)

ስላደረገልኝ እጅግ ብዙ ውለታ

አመልከዋለሁኝ ሳልሰለች ለአንድ አፍታ

ከዚህ ሌላ ምለው ምሰጠው የለኝም

ዘምርለታለሁ እኔስ እስከ ዘለዓለም

አምላኬን ሁልጊዜ አባርከዋለሁ

ምሥጋናው ዘወትር ዘወትር በአፌ ነው (፪x)

አቻምናን ማለፌ ሲደንቀኝ

አምናን በምህረትህ አለፍኩኝ

ለዘንድሮም ቢሆን አልፈራም

ጌታ ከእኔ ጋር ነህ አልሰጋም (፫x)

ጌታ ከእኔ ጋር ነህ አልሰጋም (፫x)

ጌታ ከእኔ ጋር ነህ አልሰጋም

እጅግ ብዙ ውለታ ለነፍሴ

አድርገህላታል ኢየሱሴ (፪x)

አሳቤን ጭንቀቴን ወስደሃል

አምላኬ አሳርፈኸኛል

በሕይወቴ ልትኖር መርጠሃል

የእኔንም ምሥጋና ወድሃል (፪x)

የእኔንም ምሥጋና ወደሃል መርጠሃል መርጠሃል

የእኔንም አምልኮ መርጠሃል

እጅግ ብዙ ውለታ ለነፍሴ

አድርገህላታል ኢየሱሴ (፮x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ